በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት እንዲፈርስ እና የአማራ ክልል ባንዲራ/ሰንደቅ አላማ/ እንዲቀየር ተወሰነ        አሻራ ሚዲያ   ታህሳስ 10/201…

በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት እንዲፈርስ እና የአማራ ክልል ባንዲራ/ሰንደቅ አላማ/ እንዲቀየር ተወሰነ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 10/201…

በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት እንዲፈርስ እና የአማራ ክልል ባንዲራ/ሰንደቅ አላማ/ እንዲቀየር ተወሰነ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 10/2013 ዓ•ም ባህርዳር በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ከተማ በተለምዶው አባይ ማዶ የሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት እንዲፈርስ እና የክልሉን ባንዲራ እንደሚቀይር የአማራ ክልል መንግስት መወሰኑን የአሻራ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል። ከውሳኔው ጋር በተያያዘ አሻራ ሚዲያ ያነጋገራቸው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎ እንደገለፁት የሰማዕታት ሀውልት ተብሎ ለዓመታት በከተማዋ ውስጥ ይቁም እንጂ የአማራን ህዝብ የማይወክል እና ይባሱኑም የተንበርካኪነት ምልክት ነበር የሚመስለው ብለዋል። የከልሉ ባንዲራም ቢሆን የህወሓት የበላይነት በነበረበት ወቅት ከህወሓት የተበረከተ እንጂ የህዝቦችን ፍላጎት ያካተተ አልነበረም ሁለቱም የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነው ህወሓት መገለጫዎች ነበሩ እንዲወገዱ በመደረጉም የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር መደማመጥ እየጀመረ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ሰዓት አባይ ማዶ ያለው የሰማዕታት ሀውልት በመፍረስ ላይ እንዳለም ለማወቅ ችለናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply