በባህርዳር ከተማ የሰለጠኑና የታጠቁ ተጠበባቂ ኃይሎች ዛሬ ወደ ግንባር በተደረገላቸው አሸኛኘት “የጎረቤትህን አጥር የነቀነቀ በቀጣይ ያንተን ቤት ሊያፈርስ መሆኑን አትዘንጋ” ሲሉ ገልፀዋል።…

በባህርዳር ከተማ የሰለጠኑና የታጠቁ ተጠበባቂ ኃይሎች ዛሬ ወደ ግንባር በተደረገላቸው አሸኛኘት “የጎረቤትህን አጥር የነቀነቀ በቀጣይ ያንተን ቤት ሊያፈርስ መሆኑን አትዘንጋ” ሲሉ ገልፀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባህርዳር ከተማ ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አደራ ጋሼ በመሸኛ መርሃ ግብሩ ተገኝተው እንደተናገሩት በከተማችን ባህርዳርና አካባቢው የሚገኘው ወጣት ሰልጥኖና ታጥቆ የአካባቢውን ሰላም ከማስከበር ባለፈ ወራሪውና አሸባሪው ጁንታ እያደረሰ ያለውን ጥፋት በመፋለም ላይ ይገኛል ብለዋል። እኒህ ዘማች ኃይሎች በአፍራሽ ኃይሉ የተቃጣብንን ጥቃት በመደምሰስ እየተደረገብን ያለው ጦርነት በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ በቂ የሆነ የትግል ቁመና ይዘው ወደ ግንባር በመዝመት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። ወረራውና አሸባሪው የትግራይ የጥፋት ቡድን የአማራ ህዝብ ጥቃት ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮዽያ ህዝብ ጠንቅ በመሆኑ ሁሉም ሊታገለው እንደሚገባም ተናግረዋል። በዛሬው ዕለትም በባህርዳርና ሳተላይት ከተሞች ከዚህ በፊት የሰለጠኑ ታጣቂዎች ፣ሚሊሾችንና ተጠባባቂ ኃይሎችን እየሸኙ መሆኑን እነዚህም ከግንባር ፊልሚያ እስከ ደጀንነት በመሰለፍ ያለማንም አስገዳጅነት ለሀገራቸው ሰላም ሲሉ የዘመቱ ናቸው ብለዋል። የባህርዳር ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ባዬ አለባቸው አጥፊውንና የጥፋት ተላላኪውን ኃይል በመደምሰስ በመላው ሰላም ወዳዱ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን ወረራና ጥቃት ከክልላችን በማስወገድ የአድዋን ዳግም ታሪክ የምናሳይበት ትግል ነው ብለዋል። እኒህ ለህልውናችንና ለሰላማችን ጠንቅ የሆኑ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን ከነተላላኪና ቅጥረኛ ባንዳዎቻቸው ለማጥፋት ህዝባዊ ማዕበሉን በትጥቅና ስንቅ ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት በመስራት ከጎናቸው የማይለይ መሆኑን ገልፀዋል። ዘማች ኃይሎች በበኩላቸው የመላው አማራ ህዝብ ሉአላዊ ክብር መደፈር ፣ሞትና ስደት እንዲሁም ሀብት ንብረት በወንበዴ መውደም እንዳንገበገባቸውና ይህን ጨካኝና ጨቋኝ ቡድን ለመደምሰስ የግል ኑሮ ፣ቤት ፣ንብረት ሳይገድባቸው በከፍተኛ ሀገራዊ ወኔ ትግሉን ለመቀላቀል ወደ ግንባር እየዘመቱ መሆኑን ተናግረዋል ሲል የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply