በባህርዳር ከተማ የሴቶችን ጥቃት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 8/04/2014 ዓ.ም በሰልፉ ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የፌደራል መስኖና ቆላማ አካባባቢ ሚኒስ…

በባህርዳር ከተማ የሴቶችን ጥቃት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 8/04/2014 ዓ.ም በሰልፉ ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የፌደራል መስኖና ቆላማ አካባባቢ ሚኒስቴር ሚኒስተር፤ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ፣ ወ/ሮ አስናቁ ድረስ የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናት፣ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች በተገኙበት የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተከብሯል። ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የፌደራል መስኖና ቆላማ አካባባቢ ሚኒስቴር ሚኒስተር አሸባሪውና ወራሪው ቡድን አሁን እየደረሰበት ካለው ኪሳራ በላይ ትቢያ ሁኖ እንዲቀር ለሴቶች፣ ለእናቶች፣ ለህፃናት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሲሉ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግ…ንባር ድረስ በመውረድ ጦሩን እራሳቸው እየመሩ ለአስገኙት ድል ለጠቅላይ ሚኒስትር ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በመላው ኢትዮጵያ ሴቶች ስም ምስጋና አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የትግሉን ድንበር ታውቀዋለች አታግላም ድል ተጎናጽፋለች። አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በህዝብ ይሉኝታ የተመረጠን መንግስት በፈጠራ ትርክት እና በሀሰት መረጃ ለማፍረስ እና የራሳቸውን ተላላኪ መንግስት ለመመስረት የሚያደርጉት ሴራ በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ፍጹም ተቀባይነት የለውም። ይህንን ዘመቻ ለመቀልበስ እና ሀገራችን የገጠማትን ፈተና በጽናት ለመወጣት ሴቶች በግንባር ከመፋለም በተጨማሪ የተፈናቀሉትን በመደገፍ፤ የስንቅና ሀብት በማሰባሰብ፤ የደም ልገሳ በማድረግ የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ በመሆናቸው ክብር ይገባቸዋል ብለዋል። ወራሪው ቡድን በታዳጊ ህጻናት እና ሴቶች ላይ ያደረሰው ግፍና መከራ በልጆቻችን ላይ እንዳይደገም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምጻችን እናሰማለን ብለዋል። በዚህም በመልክታቸው 1/ አሁን ባለው ሁኔታ ጦርነቱ በግንባር ብቻ ሳይሆን በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጭምር ለማወናበድ የሚሞክረውን በመሆኑ 2/ በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ በመግባት እራሳችንና አካባቢያችንን ከጸጉረ ልውጦች በመጠቀም 3/ ስንቅና ትጥቅ ከማዘጋጀት በተጨማሪ ሴት እህቶቻችን ደፋሪውንና ወራሪውን ቡድን ለመፋለም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል ወደ ግንባር እንዲሄዱ መስራት 4/ በተገቢው ሁኔታ የዘማች ቤተሰቦችን መጠየቅ እና መንከባከብ 5/ በግንባር ለሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች የሚሆን የደም ልገሳ ማድረግ ይገባል ሲሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አሸባሪውና ወራሪው ቡድን ሴቶችን እና ህጻናት እንዲሁም አረጋዊያንን ማጥቃት እንደ አንድ የጦር መሳሪያ አድርጎ የጥፋት በትሩን አሳርፏል፤ በአፋርና በአማራ ክልል በርካታ ሴቶች እና ህጻናት እንዲሁም አረጋዊያን ተደፍረዋል፤ በአስከፊ ሁኔታ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። ምዕራባዊያንን የዚህን ወራሪ ኢሰባዊ ድርጊት ከመቀዋወም ይልቅ የሀገራችን ጉዳት ወደኋላ በመተው ለቅሷችንን በመቀማት የአሸባሪውና ወራሪውን ቡድን በመደገፍ ሰቆቃችንን ለማራዘም እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል። ወ/ሮ አስናቁ ድረስ በበኩላቸው በሽብርተኛውና ወራሪው ሀይል ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ አንግቦ በእብሪትና በማናለብኝነት በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ነገሮችን ፈጽሟል። በዚህም በቀዳሚነት ሴቶችና ህጻናት ለሞት፤ ለከፋ ርሀብ እና አስከፊ ሰብዓዊ ጥሰት ተዳርገዋል ብለዋል። ይህንን የህዝባችን ሰቆቃ እንዳላዮ የሚያልፉ፤ አሸባሪውን ቡድን በእጅ አዙር የሚደግፉ ሀያላን ሀገራት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ድምጻችንን እንዲሰሙ መልዕክት እናስተላልፋለን ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply