በባህር ዳርና ጎንደር የጁንታው ታጣቂ ሃይል በሮኬት ያደረሰው ጥቃትም ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑን አረጋግጠናል አለ።         አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ 01 /2…

በባህር ዳርና ጎንደር የጁንታው ታጣቂ ሃይል በሮኬት ያደረሰው ጥቃትም ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑን አረጋግጠናል አለ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 01 /2…

በባህር ዳርና ጎንደር የጁንታው ታጣቂ ሃይል በሮኬት ያደረሰው ጥቃትም ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑን አረጋግጠናል አለ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 01 /2013 ኣ.ም ባህር ዳር የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መርማሪ ቦርድ የመስክ ምልከታ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትዛሬ ታህሳት 01 ቀን 2013 ዓም ባቀረበበት ወቅት … መርማሪ ቦርዱ የህወሃት ጁንታ ታጣቂ ሃይል ጥፋት ባደረሰባቸው የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ምልከታ ማድረጉን አስታውቋል። የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ በሪፖርታቸው የህወሃት ቡድን የፈፀመው ተግባር አሰቃቂ፣ ጭካኔ የተሞላበትና በዓለም አቀፍ ወንጀል ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።“በባህር ዳርና ጎንደር የጁንታው ታጣቂ ሃይል በሮኬት ያደረሰው ጥቃትም ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑን አረጋግጠናል” ብለዋል። ጁንታው በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈፀመው የጅምላ ግድያና የሰሜን እዝ አባላትን በማፈን የፈፀመው ድርጊትም የአገር ክህደትና አሰቃቂ ጥቃት እንደነበር ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል። በተለያዩ ሆስፒታሎች ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ያሉ ዜጎች ተገቢው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም አቶ ለማ ገልጸዋል። መንግስት ወንጀለኞችን አድኖ በመያዝ ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመው፤ “ቡድኑ በፈፀመው ጥቃት እስካሁን ተበታትነው የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ቤተሰቦችን ለማገናኘት መስራት ይገባል” ብለዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና ሰብአዊ ድጋፎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መርማሪ ቦርዱ በሪፖርቱ አመላክቷል። ዘጋ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply