በባህር ዳር ማ/ቤት በእስር ላይ በሚገኙ የጦር መኮንኖችና ልዩ ሀይሎች ላይ ሶስተኛው ዙር የአቃቢ ህግ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ከህዳር 28 ጀምሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በባህር ዳር ማ/ቤት በእስር ላይ በሚገኙ የጦር መኮንኖችና ልዩ ሀይሎች ላይ ሶስተኛው ዙር የአቃቢ ህግ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ከህዳር 28 ጀምሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ባለ ስልጣናት ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራችኋል በሚል ተይዘው ጉዳያቸው በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት እየታዬ ያለ የአማራ ልዩ ሀይሎችና የጦር መኮንኖች ፍ/ቤት እየቀረቡ በመጀመሪያና በሁለተኛው ዙር ቀርበው ቃላቸውን የሰጡ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ተከታትለዋል። አቃቢ ህግ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 11 ከዛም ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ያስመሰከረ ሲሆን እስካሁን 52 የሚሆኑ የአቃቢ ህግ ምስክሮች መሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የአቃቢ ህግ የምስክር ሂደት ባለመጠናቀቁ በሶስተኛ ዙር ምስክሮችን መስማቱን እንደሚቀጥል በማሳወቅ ለህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቃቢ ህግ 165 ምስክሮች አሉኝ በሚል ሂደቱን ያስቀጠለ ሲሆን ከችሎት ስንገባና ስንወጣ እንዲሁም በችሎት ውስጥ ለምስክሮች ተከሳሾችን የማሳየት ሁኔታ ይታያል በሚል ቅሬታ መቅረቡና ችሎቱም እንዲስተካከል ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply