በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በሚገኙት የጦር መኮንኖች ላይ የአቃቢ ህግ 2ኛ ዙር ምስክር የማሰማት ሂደቱ መቀጠሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በሚገኙት የጦር መኮንኖች ላይ የአቃቢ ህግ 2ኛ ዙር ምስክር የማሰማት ሂደቱ መቀጠሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በሚገኙት የጦር መኮንኖች ላይ የአቃቢ ህግ 2ኛ ዙር ምስክር የማሰማት ሂደቱ መቀጠሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ላይ የአቃቢ ህግን ምስክር የማሰማት ሂደት ከመስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት ድረስ መከናወኑና በዚህም አቃቢ ህግ 26 ምስክሮችን ማሰማቱ ይታወቃል። ሁለተኛው ዙር የምስክር መሰማት ሂደትም ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ እንደሚቀጥል መገለፁ ይታወሳል። በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮንኖች ላይ የአቃቢ ህግ 2ኛ ዙር ምስክር የማሰማት ሂደት ቀጥሎ እስካሁን 30 ምስክሮች ተሰምተዋል። ከጥቅምት 30 ጀምሮ እስከ ዛሬ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አቃቢ ህግ 4 የፀረ ሽምቅ አባላትን ማስመስከሩና ዛሬ ከሰዓትም እንደሚቀጥል ተገልጧል። በአምሳ አለቃ አበበ መልኬ ይመሰክራል በሚል የቀረበው የፀረ ሽምቅ አባል መሆኑ የተገለፀው አውሎም ተመስገን ሲሆን አበበ መልኬን እንደሚያውቀው ለችሎቱ የተናገረ ቢሆንም የሚያውቀው ከሆነ ለይቶ እንዲያሳይ ተጠይቋል። 3 ጊዜ እድል ተሰጥቶት ሙከራ አድርጓል፤ በወቅቱም ከአበበ ይልቅ ሌሎችን በመጠቆሙ እንዲቀመጥ ተደርጓል። ችሎቱም “መለየት አልቻልክም፣ በምን አውቀኽው ነው? አውቃለሁ ብለህ የተናገርከው?” ተብሎ ሲጠየቅም መርማሪዎች ማ/ቤት ወስደው ስላሳዩኝና በፎቶም ስላሳዩኝ ጭምር ስለማለቱ ተገልጧል። ከአቃቢ ህግ ምስክሮች መካከልም እንደአብነት በአምሳ አለቃ አበበ መልኬ ላይ የመሰከረውን ለመመልከት ተችሏል። አቃቢ ህግ አምሳ አለቃ አበበ መልኬን ለምስክር በጣቱ ሲጠቁም አይቻለሁ በማለት ለዳኛ በተከሳሽ በኩል ተቃውሞ ቀርቧል። “ድሮ በውሸት በማስመስከር ወያኔ በተቆጣጠረው ፍ/ቤት ታፍነን ቆይተናል፤ ያ ጊዜ አልፏል! መደገም የለበትም! አሁንም አቃቢ ህግ ሆን ተብሎ ሰውን በግድ እወቅ እያለ ነው? ውጭ ላይ ስንገባም ሆነ ከእዚህም እየጠቆሙ ነው፤ የሀሰት ምስክር መቆም አለበት!” በማለት አምሳ አለቃ አበበ መልኬ መናገሩና ሌሎች ተከሳሾችም ተመሳሳይ ቅሬታ ስለማሰማታቸው ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በተከሳሾች የተነሳውን ቅሬታ አግባብነት በመቀበል አቃቢ ህግ ማስተካከያ እንዲያደርግ ትዕዛዝ ስለመስጠቱ ተገልጧል። አቃቢ ህግ 165 ምስክሮች አሉኝ በማለቱ ምስክር የማስደመጥ ሂደቱ እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply