You are currently viewing በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ  በሰኔ 15/2011ዱ የባለ ስልጣናት ግድያ ተከሰው በተሰጠው ፍርድ ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኝ የጠየቁት የጦር መኮንኖች መዝገብ “ያስቀርባል…

በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ በሰኔ 15/2011ዱ የባለ ስልጣናት ግድያ ተከሰው በተሰጠው ፍርድ ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኝ የጠየቁት የጦር መኮንኖች መዝገብ “ያስቀርባል…

በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ በሰኔ 15/2011ዱ የባለ ስልጣናት ግድያ ተከሰው በተሰጠው ፍርድ ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኝ የጠየቁት የጦር መኮንኖች መዝገብ “ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም” በሚለው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በፕላዝማ ችሎት ሊቀርብ ነው። ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሰኔ 15/2011ዱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ወንጀል ተከሰው በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙትና የተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለታቸው ይታወሳል። እየታዬ ነው በሚል በርካታ ወራትን ያስቆጠረው ይህ የይግባኝ መዝገብ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ አግባብነት የለውም በሚል ነው ቅሬታ የቀረበበት። በዚህም መሰረት የይግባኙ መዝገብ በ3 ተከፍሎ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ከመዝገቡ የገጽ ብዛት አንጻር እየታዬ ነው በሚል በርካታ ወራትን አስቆጥሯል። በአጠቃላይ ይግባኝ የጠየቁት 29 ሰዎች ሲሆኑ 25ቱ በአንድ መዝገብ_ በእነ ሻምበል ውለታው አባተ፣ ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ በእነ ሻምበል ታደሰ እሸቴ የሚጠራ መዝገብ የከፈቱ ሲሆን ሶስተኛው መዝገብ አምሳ አለቃ አበበ መልኬ ለብቻው ያቀረበው ይግባኝ መሆኑ ተመላክቷል። የይግባኝ መዝገቡ “ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም”፣ “ያከራክራል ወይስ አያከራክርም” በሚለው ጉዳይ ላይ ለውሳኔ በሚል ዛሬ ጥቅምት 11/2015 ተቀጥሯል። በዚህም መሰረት ዛሬ ጥቅምት 11/2015 ረፋድ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባ/ዳር የፕላዝማ ማስተባበሪያ ችሎት ላይ ዳኝነቱ እንደሚሰማ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጠበቃ ህሩይ ባዬን አነጋግያቸዋለሁ በማለት እሳቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ችሎቱ ያስቀርባል ካለ ለጠቅላይ አቃቢ ህግ መጥሪያ በመስጠት በጦር መኮንኖች የይግባኝ አቤቱታ ላይ የጽሁፍ ምላሽ እንዲያቀርብ ይደረጋል፤ በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ከተደረገበት በኋላም ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል። ፎቶው የአምሳ አለቃ አበበ መልኬ ነው። ምንጭ:- አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply