You are currently viewing በባህር ዳር በእስር ላይ የሚገኙት ስንታየሁ ቸኮል፣ ያለለት ወንድዬ፣ ደምስ አያሌውና ዋሴ ቢረሳው በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ፤ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የታፈኑት ተማሪዎች ከኢትዮ 360 ጋር ግንኙ…

በባህር ዳር በእስር ላይ የሚገኙት ስንታየሁ ቸኮል፣ ያለለት ወንድዬ፣ ደምስ አያሌውና ዋሴ ቢረሳው በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ፤ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የታፈኑት ተማሪዎች ከኢትዮ 360 ጋር ግንኙ…

በባህር ዳር በእስር ላይ የሚገኙት ስንታየሁ ቸኮል፣ ያለለት ወንድዬ፣ ደምስ አያሌውና ዋሴ ቢረሳው በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ፤ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የታፈኑት ተማሪዎች ከኢትዮ 360 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል እየተንገላቱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኢትዮ- 360 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታፈናቸው ተገልጧል። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት፣ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ አምስት ተማሪዎች ታፍነዋል። ተማሪዎችን ለእስር ያበቃቸው አንደኛው ምክንያት “ከኢትዮ 360 ጋር ግንኙነት አላችሁ” የሚል ነው። በተማሪ ኤርሚያስ ጥጋቤ እና መኳንንት ሙላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል። ህክምና እናዳያገኙም ተደርጓል። የታገቱት ተማሪዎች ጎንደር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። የታፈኑት ተማሪዎች ስም ዝርዝር:_ 1 ኤልያስ መኩሪያው 2 አምበሉ ክበር 3 ኤልያስ ስራዬ 4 ሰለሞን ዋርካው 5 አቤኔዘር ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በባህር ዳር በእስር ላይ የሚገኙት ስንታየሁ ቸኮል፣ ያለለት ወንድዬ፣ ደምስ አያሌውና ዋሴ ቢረሳው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ተወስኗል። እንዲሁም፣ በአዲስ አበባ ያሉት ታዲዮስ ታንቱም በ15 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ባልደራስ ነው ያጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply