
በባህር ዳር ከተማ ታላቅ ኦርቶዶክሳዊ ሰልፍ እና ጸሎተ ምህላ ሊካሄድ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የፊታችን እሁድ ጥር 28/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ በባሕር ዳር መስቀል አደባባይ (ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም) ሁሉም ምእመን ከአጥቢያው በኅብረት 1:00 ላይ ተነሥቶ 1:30 ላይ መስቀል አደባባይ ይደርሳል። አዘጋጅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የባ/ዳር ሀገረ ስብከት መሆኑ ተገልጧል። በእለቱም በኮሚቴው ከተዘጋጁ ባነሮች ውጭና ያልተፈቀዱ መልእክቶችን ይዞ መምጣትና ማስተላለፍ የተከለከለ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዐርማ ውጭም ምንም ነገር መያዝ አይፈቀድም ተብሏል።
Source: Link to the Post