You are currently viewing በባህር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች መሬታቸው አላግባብ በከተማ አስተዳደሩ እንደተወሰደባቸው ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል  ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ. ም…

በባህር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች መሬታቸው አላግባብ በከተማ አስተዳደሩ እንደተወሰደባቸው ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ. ም…

በባህር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች መሬታቸው አላግባብ በከተማ አስተዳደሩ እንደተወሰደባቸው ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ እንደሚኖሩ የገለጹ አርሶ አደሮች ለበርካታ ዓመታት በህጋዊ መንገድ ይዘው ሲገለገሉበት የቆዬ መሬታቸው በከተማ አስተዳደሩ አላግባብ እንደተወሰደባቸው የሚያመለክት ቅሬታቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል አቅርበዋል። በከተማ መስፋት ምክንያትም ሆነ መንግስት ይገባቸዋል በሚል ለተደራጁ የተለያዩ ማህበራት የእርሻ መሬታችን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት የእኛ የአርሶ አደሮችን መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት ማስከበር ይኖርበታል ብለዋል። ኮሚቴ አዋቅረው እየታገሉ መሆናቸውን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በህጋዊ መንገድ ሲያለሙበት የኖረው መሬታቸው አሁን ላይ ያለምንም ካሳ ከተማ አስተዳደሩ ባሰማራቸው ሚሊሾች እየተጠበቀ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በመሆኑም በክረምት አርሰው የሚያለሙት እንዳለ ሆኖ በብዙ መስዋዕትነት ከተከሉት ቋሚ አትክልት እንኳ መጠቀም አልቻሉም። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በዘንዘልማ አርሶ አደሮች የተነሳውን ቅሬታ መሰረት በማድረግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባን አቶ ባዬ አነጋግሯል። አቶ ባዬም በቅድሚያ ግብርና ምን ምላሽ ሰጠ? በማለት ለአሚማ ጥያቄ አንስተዋል፤ ከግብርና ምላሽ በኋላ ሂደቱን ጠብቀው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። በዚህም አሚማ የግብርና እና ገጠር መሬት መልሶ ማቋቋም መምሪያ ኃላፊን አቶ ትልቅሰውን ያነጋገረ ሲሆን ኃላፊውም ጉዳዩን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ሲከታተሉት የቆዩት አቶ ባዬ ስለሆኑ ወደ ሌላ መግፋት ተገቢ አይደለም በማለት እሳቸውም ወደ ከተማ አስተዳደሩ መልሰው ገፍተውታል። በተጨማሪም ከገጠር መሬት አስተዳደር የሀብት ዋጋ ተመንና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክተርና ተወካይ የሆኑት አቶ ምስጋናው አባተ በበኩላቸው አርሶ አደሮች የሚያነሱት ቅሬታ በአብዛኛው ትክክል መሆኑን ተናግረዋል። መሬታችን ተለክቶ ለሌላ ወገን ሲሰጥ የጭስ ቤታችን ባይነካም መሬት ሊሰጠን ይገባል የሚለውን ግን መመሪያን የሚጣረስ በመሆኑ እንደማይቻል ተነጋግረናል ብለዋል ዳይሬክተሩ። ከዚህ ባሻገር ግን በተደጋጋሚ እየቀረበ ያለው የዘንዘልማ አርሶ አደሮች ቅሬታ ምላሽ ያገኝ ዘንድ ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መስተካከል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ደብዳቤ የጻፍን ቢሆንም እስካሁን ለማስተካከል አልተቻለም ብለዋል። እንደአብነትም ከአርሶ አደሮቹ የመሬት ባለቤትነት ደብተር ጋር በተያያዘ፣ በሌለንበትና ያለመተማመኛ ፊርማ የመሬት መወሰድ፣ በእርሻ ማሳቸው ላይ ስላለው ፍሬ ያለው የቋሚ አትክልት አገማመት ጉዳይ፣ የካሳ ጉዳይና ሌሎችንም ከመመሪያ አኳያ ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮችን በተመለከተ በደብዳቤው ጭምር ለተቋሙ ስለመላካቸው አቶ ምስጋናው ገልጸዋል። አሚማ በድጋሜ ያነጋገራቸው የባህር ዳር ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ባዬ በበኩላቸው ከገጠር መሬት ተላከ የተባለው ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው አስተባብለዋል። የካሳ ግምት መሰራቱንና ከወቅቱ አንጻር የክልሉ መንግስት ያዝ አድርጉት የሚል አቅጣጫ በመስጠቱ ሂደቱ ለጊዜው መቆሙን ተናግረዋል። አርሶ አደሮቹ እስር፣ ድብደባ እና ወከባ ደርሶብናል ካሉ በህግ አግባብ መጠየቅ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። የአርሶ አደሮቹ መብትና ጥቅም እንዲከበር ግን አሁንም እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸው ከአርሶ አደሮቹ ይልቅ ግን በህገ ወጥ ግንባታ የተሳተፉ ሌሎች አካላት ባልተገባ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን እየተንቀሳቀሱ ስለመሆኑ ጠቁመዋል። በመጨረሻ ግን የተደራጁ ማህበራትንና አርሶ አደሮችን የማያስታርቅ ስራ እንደማይሰራ ተናግረዋል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply