
በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የአማራ ወጣቶች ማህበር አባላትና የከተማው ወጣቶች በመተከል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ድጋፍ አሰባሰቡ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-23/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የአማራ ወጣቶች ማህበር አባላትና የከተማው ወጣቶች በመተከል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የተለያዩ ድጋፎችን መሰብበባቸውን ገልጸዋል፡፡ በመተከል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ተለይተው ከኖሩበት ቀያቸው እንዲፈናቀሉና ብዙግፍ አንዲደርስባቸው ተደርገዋል፡፡ የድጋፉ አስተባባሪወች እንደገለጹት በአሁኑ ሰዓት ተፈናቃዮች ችግር ላይ ይገኛሉ ብለወል፡፡ በዚህም ምክንያት ወገኖቻችንን ለመረዳትና ድጋፉን ለማሰባሰብ ተነሳስተናል ብለዋል፡፡ በድጋፉ ላይ ከህጻን እስከ አዋቂ እንደተሳተፉበት ያነጋገርናቸው የድጋፉ አስተባባሪዎች ተናገረዋል፡፡ እንደተሳታፊዎች ገለጻ ከመተከል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በተለያየ አይነት የምግብ ፍጆታ ለአብነትም ያህል መኮረኒ፣ፓስታ፣ሩዝ፣ዱቄት ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሀ እንዳሰባሰቡላቸው ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን የተፈናቃዮች ቁጥር ብዙ ስለሆነ የተሰበሰበው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ ያነጋገርናቸው የድጋፉ አስተባባሪወች ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስላሉ መንግስት በአስቸኳይ ሊደርስላቸው ይገባል ብለዋል የድጋፉ አስተባባሪወች፡፡ በመጨረሻም ህብረተሰቡ በሚችለው አቅሙ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ
Source: Link to the Post