You are currently viewing በባህር ዳር ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ የምደረ ገነት ቀበሌ ነዋሪዎች ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ኃይል ፋኖና ሚሊሻ በማህበረሰቡ ትብብር የኃላ ደጀንነትን…

በባህር ዳር ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ የምደረ ገነት ቀበሌ ነዋሪዎች ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ኃይል ፋኖና ሚሊሻ በማህበረሰቡ ትብብር የኃላ ደጀንነትን…

በባህር ዳር ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ የምደረ ገነት ቀበሌ ነዋሪዎች ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ኃይል ፋኖና ሚሊሻ በማህበረሰቡ ትብብር የኃላ ደጀንነትን አጠናክሮ ለመቀጠል የስንቅ ዝግጂት እያካሄዱ ነው፡፡ አሻራ ሚዲያ(ህዳር 18/2014 ዓ.ም) ከዘመናት በፊት ሀገራችንን ለመውረር የመጣውን የጣልያን ወራሪ ኃይል አንድ ልብ አንድ ክንድ በመሆን በመጣበት እንዳይመለስ በአለበት እንዲደመሰስ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወንድ ሴት ሳይሉ በመተባበር ወራሪውን በመቅብር ያልተደፈረች ነጻነቷ የተከበረች ሀገር አባቶቻቸን እስረክበውናል፡፡ አሁን የውጭ ወራሪ ፈርቶና አከበሮ ታሪኳን እየዘከረላት የተቀመጠችዋን ሀገረ ኢትዮጵያን ከጉያዋ ተወልዶ ያደገው አሸባሪው ኃይል ሀገሪቱን ለመበተን ሲኦል ድረስ እዘልቃለሁ የሚለውን ቀረርቶውን ከመነሻ…ው በማፈንና የተልዕኮ እጆቹን በመሰባበር ህልሙን ለመበታተን ውድ ኢትዮጵያዊያን ለሀገሬ ያልሆነች ነፍስ ለእኔ ምኔ ነች ብለው በህብረት ተነሳስተዋል፡፡ ሰራዊቱ ልዩ ህይሉና ሚኒሻው በግንባር ለአንዲት ኢትዮጵያ ሲዋደቅ የኋላው ማህበረሰብ የሎጂስቲክስ አቀራቢነቱን አጠናክሮ እየቀጠለ በአለበት በዚህ ሰአት የባህር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ምደረ ገነት ቀበሌ ነዋሪዎች አጋርነታቸውን አጠናከረው ለመቀጠል የስንቅ ዝግጂት እያደረጉ ነው፡፡ በክፍለ ከተማው እየተካሄደ ያለውን የስንቅ ዝግጂት በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የስንቅ ዝግጂት ሰራው በሁሉም ክፍለ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን በመጠቆም ማህበረሰቡ እያሳየው ያለው ተነሳሽነት ለሰራዊቱ ሞራል ጭምር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ ወደ ግንባር ዘምተው የሚዋጉ አመራሮች አሉ ያሉት ዶ/ር ድረስ ቀሪው አመራር የሎጆስቲክስ ስራውን ማህበረሰቡን በማንቃት አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፍየ ኩራባቸው ከ3 ሚሊዮን ብርና በአይነት ከ3 መቶ ኩንታል በላይ ስንቅ ለሰራዊቱ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ማህበረሰቡ ያለውን ሳይሰስት በማዋጣት ድጋፉን መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ በስንቅ ዝግጂት ስራው ላይ እየተሳተፉ ያገኘናቸው እናቶች ልጆቻችን ልዩ ሃይልና መከላከያን ተቀላቅለዋል ብለዋል፡፡ ለሰራዊቱ ከኃላ ደጀን ከመሆን ባለፈ ግንባር ላይ በመሰለፍ ወራሪውን ኃይል ለማስወገድ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በክፍለ ከተማው እየተካሄደ የሚገኘውን የድጋፍ ስራ የሚያስተባብሩ ወጣቶች የነዋሪው ድጋፍ ግንባር ለሚገኘው ኃይል ጉልበት እየሆነ ነው በማለት ወጣቶቹ በከተማው በመዘዋወር ድጋፍ እያሰባሰቡ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዘጋቢ፡- አማኑኤል ካሰው

Source: Link to the Post

Leave a Reply