በባህር ዳር ከተማ የጦር መኮንኖችን የምስክር ሂደት ሲከታተል የነበረው የአለም አቀፉ የአማራ ሕብረት ዋና ጸሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ መታሰሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳ…

በባህር ዳር ከተማ የጦር መኮንኖችን የምስክር ሂደት ሲከታተል የነበረው የአለም አቀፉ የአማራ ሕብረት ዋና ጸሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ መታሰሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳ…

በባህር ዳር ከተማ የጦር መኮንኖችን የምስክር ሂደት ሲከታተል የነበረው የአለም አቀፉ የአማራ ሕብረት ዋና ጸሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ መታሰሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአለም አቀፍ አማራ ሕብረት ም/ሊቀመንበር አማረች አስራቴ እንደገለፀችው የማህበሩ ዋና ጸሀፊ የጦር መኮንኖችን ችሎት ለመታደም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከሄደበት በፖሊስ አባላት ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዶ ታስሯል። ከሰኔ 15ቱ በአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራችኋል በሚል በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት የታሰሩት የጦር መኮንኖችና የልዩ ሀይል አባላት ሁለተኛ ዙር አቃቢ ህግ ምስክር ከጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ህዳር 2 ቀን 2013 ዓም የነበረውን የምስክር ሂደት ለመታደም ወደ ክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀናው ወጣት መሳፍንት መንግስቱ ከችሎት ሲወጣ በአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን አባላት ተይዞ በ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ተገልጧል። የማህበሩ ም/ሊቀመንበር እንደገለፀችው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያሰረው የአደራ እስረኛ ነው በሚል እስካሁን ፍ/ቤት አልቀረበም። ችሎት መታደም ወንጀል አይደለም፤ ወንጀል ሰርቷል ከተባለም ህጉ በሚፈቅደው አግባብ ፍ/ቤት መቅረብ ሲገባው በአደራ መልክ አስሮ ማስቀመጥ ተገቢ ነው ብላ እንደማታምን የህብረቱ ም/ሊቀመንበር ገልጻለች። ከጦር መኮንኖች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ችሎት ለመታደም የመጣው መሳፍንት መንግስቱ አላግባብ ታስሮብናል የሚል ቅሬታ በእስር ላይ ባለው የአዴሃን አመራር በሆነው በአቶ ስለሽ በኩል ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቧል። ችሎቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረትም ከፖሊስ ኮሚሽን ኮማንደር አለምነው አዳሙ ቀርበው ችሎት ለመታደም የመጣውን መሳፍንት መንግስቱን ለምን እንዳሰሩ ሲጠየቁ ችሎት ተከታትሎ በፌስ ቡክ ላይ በመጻፉ ነው ስለማለታቸው ተገልጧል። አቶ ስለሽም ችሎቱ እየደረሰብን ያለውን ተደራራቢ በደል ይገንዘብልን ስለማለቱና ችሎቱም እንዲህ ዓይነት ነገሮች መታረም እንዳለባቸው አሳስቧል ተብሏል። አቃቢ ህግ እስከ ትናንት ድረስ 36 ምስክሮችን አቅርቦ ስለማስደመጡና ዛሬም የሚቀጥል ስለመሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply