You are currently viewing በባህር ዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው አሸናፊ አካሉ አሁን ላይ ወደየት እንደተወሰደ  አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

በባህር ዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው አሸናፊ አካሉ አሁን ላይ ወደየት እንደተወሰደ አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

በባህር ዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው አሸናፊ አካሉ አሁን ላይ ወደየት እንደተወሰደ አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች አባል እና የምዕራብ ጎጃም ዞን አመራር በመሆን ስለሰፊው የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ትግል በማድረግ የሚታወቀው አሸናፊ አካሉ ጥር 7/2015 መታሰሩ ይታወቃል። በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከባለእግዚአብሔር ጀርባ ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤቱ ጥር 7/2015 ከቀኑ 10:30 ገደማ በመጡ ቁጥራቸው ከ20 የማያንሱ የአድማ ብተና አባላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ታፍኖ ወደ ባህር ዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ታስሮ የነበረው አሸናፊ አካሉ አሁን ላይ ወደየት እንደተወሰደ አለመታወቁ ተገልጧል። ሌሊት ላይ በፓትሮል ከእስር ቤት አስወጥተው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዱ የሚናገሩት ምንጮች ቤተሰቦቹ አድራሻው እንዲነገራቸው ቢጠይቁም ፈቅዶ ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም ተብሏል። በባህር ዳር የተለያዩ እስር ቤቶች እየዞሩ ሲፈልጉ ቢውሉም የአሸናፊ አካሉን አድራሻ ለማወቅ አለመቻላቸው ተገልጧል። ይህም ቤተሰቡን ለከፍተኛ ጭንቀት መዳረጉ ታውቋል። እንደዚህ ዓይነት የብልጽግና አገዛዝ የአፈና አካሄድ ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply