በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች “መንግስት አሁንም በወለጋ ያለው የቤተሰቦቻችን እልቂት ጉዳይ እያሳሰበው አይደለም” ሲሉ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 6 ቀን 2014…

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች “መንግስት አሁንም በወለጋ ያለው የቤተሰቦቻችን እልቂት ጉዳይ እያሳሰበው አይደለም” ሲሉ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤተሰቦቻችን ላይ ከሰሞኑ ብቻ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ንጹሃን ተገድለዋል፤ አካላቸው የጎደሉና ህክምና ያጡ ወገኖቻችን ጉዳይም ያሳስበናል ብለዋል። በኦሮሚያ ያሉ የመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዜያት የሚሰጡት መግለጫም ክህደት የተሞላበት በመሆኑ እንደሚያሳዝናቸው ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ሲቀጥሉ የባለስልጣናቱ ምላሽ የሚያመለክተው ቡድኑ ለሚፈጽመው ጭፍጨፋ ሽፋን በመስጠት ላይ ስለመሆናቸው ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ነሃሴ 12 ቀን 2013 እና መስከረም 30 ቀን 2014 በኪረሞ ወረዳ በመርጋ ጅሬኛ እና በሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌዎች ቀድመው ልዩ ኃይሉን እንዲወጣ በማድረግ በአማራዎች ላይ ጭፍጨፋ ያስፈጸሙት የመንግስት አመራሮች ናቸው ሲሉ ይከሳሉ። “መንግስት አሁንም በወለጋ ያለው የቤተሰቦቻችን እልቂት ጉዳይ እያሳሰበው አይደለም” የሚሉት ተማሪዎቹ በእውኑ ለዜጎች የሚቆረቆር ከሆነ በአስቸኳይ ወርዶ መዋቅሩን መፈተሽ አለበት፤ ሰብአዊ እርዳታም ማድረስም ይኖርበታል ይላሉ። ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚማሩ መሆናቸውን የገለጹት ተማሪዎቹ ወደ ምስራቅ ወለጋ ተመልሰው ከቤተሰባቸው ጋር ለመገናኘት ባለመቻላቸው ለዘርፈ ብዙ ችግር መዳረጋቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። በመሆኑም መንግስት የወለጋን አካባቢ ሰላም ለማስፈን ካልቻለና ካልፈለገ መንገዱ ተከፍቶ ቤተሰቦቻችን በሰላም እንዲወጡ እንዲያደርግ እንማጸናለን ብለዋል። በተያያዘ በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ከተማ ቦትሮ ቦራ መውጫ ልዩ ስሙ ጎማጣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ አካባቢ ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2014 ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ የሽብር ቡድኑ ተኩስ መክፈቱ ተሰምቷል። የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድኑ ከዛሬው ጋር ለሶስተኛ ቀን በምሽትና በሌሊት እየመጣ በሚሊሾች ላይ ተኩስ በመክፈት አቅማቸውን እየለካ መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply