በባልደራስ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የራስ ገዝነት ጥያቄ ዙሪያ በመምከር የጋራ ኮሚቴ ያዋቀሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በማይካድራ በአማራ ተወላጆች ላይ የተደረገውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በፅኑ…

በባልደራስ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የራስ ገዝነት ጥያቄ ዙሪያ በመምከር የጋራ ኮሚቴ ያዋቀሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በማይካድራ በአማራ ተወላጆች ላይ የተደረገውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በፅኑ አውግዘው በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ መሰረቱ በባልደራስ መሪነት በፓርቲዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የራስ ገዝነት (አድያምነት) ጥያቄ በትላንትናው ዕለት በፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ለሶስተኛ ጊዜ ነባር እና አዳዲስ ፓርቲዎችን ጨምሮ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዕለቱ የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ባልደራስን ጨምሮ 6 ፓርቲዎች ተገኝተዋል፡፡ በመድረኩ በዋና አጀንዳነት የአዲስ አበባ የራስ ገዝነት ጥያቄን አስመልክቶ የጋራ ኮሚቴ ማቋቋምን የተመለከተ ቢሆንም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዬች ላይ በተጨማሪነት ተወያይተዋል፡፡ ይህንም አስመልክቶ ህወሐት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ አውግዘዋል፡፡ በማይካድራ በአማራን ተወላጆች ላይ የተደረገውን የዘር ማጥፋት በፅኑ ኮንነው በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ በትህነግ ላይ እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃም ደግፈዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በስተመጨረሻ የአዲስ አበባን የራስ ገዝነት ጥያቄ በባልደራስ መሪነት በተቀናጀ መልኩ ለማስሄድ ይረዳ ዘንድ የጋራ ኮሚቴ መስርተዋል፡፡ ኮሚቴው በቀጣይ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተገናኝቶ የአሰራር መመሪያዎችን በማዘጋጀ ወደ አፈፃፀም እንዲገባ ተወስኖ በዕለቱ በተለያየ ምክንያት ላልተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ እንዲሳተፉ ጥሪ እንዲደረግላቸው ተወስኗል ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply