በባቱ ሃይቅ የአሳ ምርት መቀዝቀዙን በአከባቢው የሚገኙ የአሳ አስጋሪዎች ተናገሩ በባቱ ሀረ ደንበል ወይንም ዝዋይ ሃይቅ የአሳ ምርት ከዕለት ዕለት የምርቱ መቀነስ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/KzKCvRQ9ZNSCplVgvzWI7ihGey0za8IVwUdusrLw7xNWSGJ_PhkWMhSi4C-ermyuMYa96ddexTYFtpYsqMwaMcnkdAzw9gX2erzyYoIU49Iu001U2cE6DFLKugb3mezX1X4jaRvKA27hIdE3wngW3olttciZxsl3sEeuNq7AJhbH9kVjVoJ3Vt7Bg5NvXX4ahXReQjyf5cuL8coVEDA-2naOfr0QtiuPNYJdle6RcBOWFZZgZTRoP0EvRp6SQlpLB1BZ0eF-4cCCQu8nkZGiwmBZz91lrxWBtzDx1KpmNEoD08JxuPo4iybTxlrjPSVszkY-CD8akoi2CWMTmLUtMg.jpg

በባቱ ሃይቅ የአሳ ምርት መቀዝቀዙን በአከባቢው የሚገኙ የአሳ አስጋሪዎች ተናገሩ

በባቱ ሀረ ደንበል ወይንም ዝዋይ ሃይቅ የአሳ ምርት ከዕለት ዕለት የምርቱ መቀነስ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው በዘርፉ የተሳተፉ አስጋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል ።

አስጋሪዎቹ ለጣቢያችን እንዳሉ በአከባቢው ላይ ያለው ህገወጥ የአሳ አውጪዎችና ከኢንዱስትሪዎች የሚወጡ ፈሳሾች ወይንማ ኬሚካል እንደምክንያት አንስተዋል ።

ሆኖም ግን አስጋሪዎቹ እንዳሉት ለአሳ ቁጥር መመናመን በጥናት የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን ነግረውናል ።

ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ መረባቸውን ሲጥሉ በኩንታል ደረጃ አሳ የሚያገኙ ሲሆን አሁን ላይ ግን በፍሬ ነው የምናገኘው ነው ያሉት።

በዚህም ወደ ሌሎች ከተማ ይላክ የነበረው አሳ ለአከባቢው ማህበረሰብ እንኳን በቂ ያለመሆኑን ነግረውናል ።

ከዚህ በተጨማሪም ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች የአሳ ማስገሪያ መረባቸው መሰረቅ ሌላኛው ችግር እንደ ሆነባቸው ሰምተናል።

ልዑል ወልዴ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply