You are currently viewing በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር ስምነነት ከተደረገ በኋላም ውዝገቡ አሁንም ቀጥሏል፤ ስምምነቱ በተባለው መልኩ የማይቀጥል ከሆነ ቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ተጋድሎዋን እንደምትቀ…

በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር ስምነነት ከተደረገ በኋላም ውዝገቡ አሁንም ቀጥሏል፤ ስምምነቱ በተባለው መልኩ የማይቀጥል ከሆነ ቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ተጋድሎዋን እንደምትቀ…

በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር ስምነነት ከተደረገ በኋላም ውዝገቡ አሁንም ቀጥሏል፤ ስምምነቱ በተባለው መልኩ የማይቀጥል ከሆነ ቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ተጋድሎዋን እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድነትን የሚሸርሽር ድርጊት ነው የተባለው የሕገ ወጥ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት፣ ወይም ራሱን “የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” ብሎ የተነሳው አካል ያስነሳው ውዝግብ እንቀደጠለ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት 3/2015 ከመንግሥት ጋር ባደረገው ውይይት፣ በእስር ላይ ያሉ ካህናትና ምዕመናንም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ማስታወሱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ካህናትም አገልግሎታቸውን በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ ከሰምምነቱ በፊት የታሰሩት ሰዎች መፈታት ሲጠበቅ፣ እስርና ወከባ በአስቸኳይ እንዲቆም ስምምነት ላይ ተደርሷል ከተባለ በኋላም ታዋቂ የቤተክርስቲያን መምህራን ታስረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ መንግሥት የቤተክርስቲያኗን ጥያቄ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የገባውን ቃል እንደመሻር የሚያዩት አካላት ተፈጥረዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት፣ መንግሥት የቤተክርስቲያኗን አንድነትና ቀኖና እንደሚያከብርና በቤተክርስቲያኗ ላይ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን እንዲያስቆም ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡ ራሱን “የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ” ብሎ የጠራው አካል፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የተቀየረ አቋም እንደሌለው አስታውቋል፡፡ በየትኛውም መንገድ ለዕርቅ ዝግጁ ብሆንም፣ በያዝኳቸው አገረ ስብከቶችና በሾምኳቸው ኤጲስ ቆጶሳት አልደራደርም ብሏል፡፡ በአንጻሩ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተወያየው የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከመንግሥት ጋር በተደረገው ውይይት የቤተክርስቲያኗን አንድነት፣ ቀኖና፣ ሕገ ቤተክርስቲያንና አስተዳደራዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል፡፡ ከመንግሥት ጋር በተደረውገው መግባባት መሰረት ሁኔታዎች የማይፈጸሙ ከሆነ፣ ቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ተጋድሎዋን እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡ ለዚህም መንግሥት ችግሩን እንዲያስተካክል የተወሰነ ጊዜ የሰጠች ሲሆን፣ ይደረጋል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍም ተራዝሞ የመንግሥትን የመፈጸምና ያለመፈጸም ሁኔታ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ኢትዮ መረጃ ኒውስ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply