በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ፡፡በአዲስ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/dv2PI4B75Gg1nwvScOrB66a7Op2sEjsC7qVP1C66_U1IULXtGRcqJJdr5kbILYeag5gQFpb8jW5oWJCvOtd-M3Csw1y9PNVl7dpNqYrAJAAiAjgPEqZh5MJl_1Zwi_EQWWkwc24i8k_xew92amxM7WBTgaPU9iyPOQ7AW8BRvUgEMlrUmbDhNzuPT5LQbQya2xqMIqiIyu5fqeV5YK65-2saKqeUvuSGTNc5VTLkHfESeceeCNkyXCxN7NdtJyIbl3zC8K-cUjiaemn4INF-x6852gDo79sOItNc9sm9udRQ8iEnz0YnwFnWr2RrjaoHrUYzUexvUIS6vYGhldUVdg.jpg

በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ፡፡

በአዲስ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል ብለዋል፡፡።

የአደጋዉን መንስኤ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡

በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ እንዲሁም የክፍለ ከተማዉ አመራሮች በአደጋዉ ስፍራ ተገኝተዉ በአካባቢዉ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ በኮንስትራክሽን ስራ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል አስፈላጊዉ የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ መስራት አስፈላጊ መሆኑን  ኮሚሽኑ ያሳስባል።

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply