
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን፣ ግልገል በለስ ከተማ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። የዐይን እማኞቹ እንዳሉት ባለፈው አርብ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ በተፈፀመው ጥቃት ቢያንስ 18 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ የትጥቅ ትግል ለማቆም የተስማሙ ታጣቂዎች መሆናቸውን የዐይን መስክሮቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Source: Link to the Post