በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ደባጤ ወረዳ በዳለቲ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአይ እማኞች ገልፀዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ደባጤ ወረዳ በዳለቲ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአይ እማኞች ገልፀዋል፡፡የክልሉ ኮማንድ ፖለስት ሊገታው ያልቻለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው ተገኝተው ሊያስቆሙተው ያልቻለው የንፁሃን ሞት አሁንም ቀጥሏል ብለዋል፡፡ከጥቃቱ አምልጠው በጋሴስ ቀበሌ ተጠልለው ያሉ እነዚህ የአይን እማኞች ታጠቂዎች ቀበሌውን ከበው በፈፀሙት ጥቃት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ለፀጥታ ሀይሎች መረጃ ብናደርስም ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት የሚደርስልን አካል አላገኘንም ብለዋል፡፡በአካባቢው ካሉ ቀበሌዎች ሸሽተው በርካታ ሰዎች በጋሌሳ ቀበሌ መጠለላቸውን ገልፀው በጋሌስ አስተማማኝ ጥብቃ እንደሌለ ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ኮሌኔል አቶ እያሌው በየነ አሁንም ድረስ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እና ግዲያ ኦነግ ሸኔን ጨምሮ ሌሎች አጥፊ ሀይሎች በማህብረሰቡ ውስጥ መቀላቀላቸው ፈተና እንደሆነባቸው ለአሐዱተናረዋል፡፡

አክለውም እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶች በቀጣናው ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ የጥራት ችግር እንደሚስተዋል ገልፀው ይህን እኩይ ተግባር የሚፈፅሙ ከህውሃት ጋር ግንኙነት ያለውን ጠላት በሙሉ ለመደመስስ ጊዜ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

ጥር 07/2013

አሐዱ ሬዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply