በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ጥቃት ለተፈናቀሉ ሴቶችና ህጻናት ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከልና አከባቢዋ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ሴቶችና ህፃናት ግምታዊ ዋጋቸው 2 ሚሊዮን ብር የሆነ አልባሳት፣ የምግብ ግብአት፣ የኮቪድ 19 መከላከልና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ለአሀዱ በላከው መረጃ ገልጿል።

በሌላ በኩል ሚኒስቴሩ 1 ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማእከል ገቢ አድርጓል። እንዲሁም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ ለሴት የሀገር መከላከያ ሰራዊት 500 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።በህግ ማስከበር ሂደት ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ ለወጣቶችና ሴቶች የተለያዩ አልባሳትና ንህፅና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

*************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply