በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመተከል የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡የቢሮው…

https://cdn4.telesco.pe/file/nTGqi-cuiQkjRT7wO1vVh0TCL8-kSbSB8S5RTnKx70dTMVpzAb0k9tP01rkqhjBFFv6DRta4N9A-8gEJNxhE5vN6uG6wO_1x8sNzvjWBNr79V3bqAx5EmG00EEyqY3HzJ3wgKSYenPhrChJhleY_fpxcu3hWODwAz3o5jfg1xwAlbY6WWvUn8wgC9dn_PggpN9Nzhl06-2UT-hNZHYR_2zcPo9J066FIpBjF8S0Tp1Y_91NRNh-0U8uEm12hos96NxTLebOyIh0tKbTsD2c5O2n9kteNG2fRtBn6Y00kZzRDX5cYC9xi1xJfqrkQ9656RBKabPGKDLoxVSN2m6nFtg.jpg

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመተከል የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ÷ዛሬ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ አንዱ ናቸው፡፡ ሌላው የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡
የዞኑ ሠላም ወደ ቀደመ ሁኔታ እስኪመለስ ከጸጥታ ችግሩ ጋር እጃቸው ያላባቸውን አመራሮች ጨምሮ ሌሎችንም ግለሰቦች የማደን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ሙሳ ጨምረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply