በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ የጤና ባለሙያዎች ውስጥ ስምንቱ ተለቀቁ።የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በ…

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ የጤና ባለሙያዎች ውስጥ ስምንቱ ተለቀቁ።

የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በክልሉ ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ ባሳለፍነው እሁድ
ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም 5 ወንድ 7 ሴት 1 አሽከርካሪ እና 1 መካኒክ በድምሩ 14 ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው ነበር።

በታጣቂዎቹ ታግተው ከነበሩት የጤና ባለሙያዎች መካከል ስምንቱ ተለቀዋል ተብሏል።

ባለሙያዎቹ የተለቀቁት የአገር መከላከያ ሰራዊት በአጋቾቹ ላይ ባደረገው እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

ከተለቀቁት ውስጥ አንደኛዋ የጤና ባለሙያ እንደተናገረችው የተቀሩት ታጋቾች ከመከላከያ ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ አምልጠው ጫካ ገብተው ነው እንጂ በጸረ ሰላም ሀይሉ አልተያዙም ብላለች።

አቶ መለስ ግን ይሄንን እርግጠኛ ልንሆን ስለማንችል ወደ ቦታው መከላከያ ሚሊሻና ፌደራል ፖሊስ በመላክ እየተፈለጉ ነው ብለውናል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት በዚህ እገታ ተሳትፈዋል ባላቸው ታጣቂዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ከ16 በላይ ታጣቂዎችን መደምሰሱ ያታወሳል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply