በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የግፍ ግድያ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የንፁሃን ደም ፈሷል፤ ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡እየተፈፀሙ ያሉት ጥቃቶችና  ግድያዎችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ ያልተቻለው ጠላት ያለው በማህብረሰቡ ውስጥ  በመሆኑ የህግ ማስከበሩን ሂደት አስቸጋሪ አድረጎታል ብለዋል የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ኮለኔል አያሌው በየነ፡፡

ሌላኛው ችግር ብለው ያነሱት ደግሞ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያለው አመራር የብቃት ማነስ ችግር ሲሆን በዞኑ ያለው ጠላት ከህውሃት የጥፋት ሃይል ጋር  ግንኙነት ያለው በመሆኑ እነኚህን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ጊዜ ይወስዳል ብለዋል የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢ፡፡ይሁን እንጂ አሁን እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለመከላከል ጥቃት አድራሾችን ህግ ፊት ለማቅረብ በተደራጀ የፀጥታ ሃይል መሰራት ተጀምሯል ብለዋል፡፡

አዘጋጅ፡ ወንድማገኝ ሃይሉ

Source: Link to the Post

Leave a Reply