You are currently viewing በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የማኦኮሞ ወረዳ በአሻጥር እንዲፈርስ ብሎም የአሸባሪዎች ነጻ መሬት እና መፈንጫ እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀም…

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የማኦኮሞ ወረዳ በአሻጥር እንዲፈርስ ብሎም የአሸባሪዎች ነጻ መሬት እና መፈንጫ እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀም…

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የማኦኮሞ ወረዳ በአሻጥር እንዲፈርስ ብሎም የአሸባሪዎች ነጻ መሬት እና መፈንጫ እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የማኦኮሞ ወረዳ ዋና ከተማ ሰንጎ ይባላል። የማኦኮማ ወረዳ የሚገኘው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን ነው። ማኦዎች እና ኮሞዎች በብዛት የሚኖሩበት፣ በርታዎች እና ሌሎች ወገኖችም በጥቂቱ የሚኖሩበት የልማት ኮሪደር የሆነ ወረዳ ነው። ይህ ወረዳ ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብሎም ለኢትዮጵያ ዋነኛ የኢኮኖሚ ዞን መሆኑን ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ይናገራሉ። የማኦኮሞ ወረዳ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከሁለት ሀገራት ማለትም ከሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ የኢኮኖሚ ዋልታ ነው። ወረዳው ከኦሮሚያ ክልል ጋርም የሚዋሰን ነው፤ እንዲያውም ክልሉ ከሰሜንና ደቡብ ሱዳን ጋር እንዳይገናኝ የጋረደው ወረዳ ስለመሆኑ ይነገራል። ይህ ወረዳ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መዋቅር ውስጥም ሆነ ከመዋቅር ውጭ ላሉ ተስፋፊዎችና ያዩትን ሁሉ ኃይልን ጨምሮ በሚችሉት መንገድ ሁሉ ለራሳቸው ከማድረግ ወደኋላ ማለትን ለማያውቁት አስደሳች ነገር አይደለም። በተለይ መዋቅራዊ ድጋፍ ያለው ዘር አጥፊው፣ ጨፍጫፊው፣ ተስፋፊው፣ አይቶም በልቶም የማይጠግበው፣ ሲያጠቁ አይቶም የማያውቀው፣ አፈናቃዩና ዘራፊው የኦነግ ሸኔ ቡድን የማኦኮሞ ወረዳን የራሱ የመንቀሳቀሻ ቀጠና ለማድረግ ቋምጧል። በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ከተሰገሰጉ የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ ጋር በመመሳጠር በአሶሳ በኩል ያለውን የቤንሻንጉልን ብሎም የኢትዮጵያን ጉሮሮ ለማነቅ በተደራጀ መንገድ እየሰራ ነው። ይህ ኃይል የተደራጀ ወራሪ አረመኔ ጦሩን ወደ ወረዳው ከማሰማራቱ በተጨማሪ ከውስጥ ካሉ የጥፋት ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን በአሻጥር እንድትፈርስ እያደረገ ነው ሲሉ ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። የኢኮኖሚ ዞን የሆነው የማኦኮሞ ወረዳ ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለይም ከታህሳስ ወር 2014 ጀምሮ ለአሸባሪዎች መፈንጫ እና ነጻ የመንቀሳቀሻ ቀጠና እንዲሆን ተደርጓል። የአካባቢው ነዋሪዎችም አብዛኞች ወረራውን ተከትሎ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለከፋ ችግር ተዳርገዋል። ይህ ወረዳ ከታህሳስ 2014 ጀምሮ በአሻጥር ሆንተብሎ በኦነግ ሸኔ ጦር ወረራ እንዲፈጸምበት፣ ተቋማት እና ሰነዶች ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙበት ተደርጓል። ከሁለት ሀገራት ጋር እንደመገናኛ ሆኖ የሚያገለግለውን የማኦኮሞ ወረዳ በኦነግ እና በውስጥ ተባባሪዎቹ ሲወረር እና ሲፈርስ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ የሆኑ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ስልጣን ወዳድ እና ሆድአደር የሆኑ ባለስልጣናት ነገር እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች በብስጭት ይናገራሉ። መሬቱን ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ጭምር ለፍርሃት፣ ለገንዘብ እና ለስልጣን በመገዛት አሳልፈው እንደሸጡት ይሰማናል ሲሉም አክለዋል። በቂ የሆነ የኃይል ስምሪት ለማድረግ ባለመፈለጋቸው ወረዳው እንደተወረረ ነው፤ የጸረ ኢትዮጵያ አሸባሪ እና ወራሪ ኃይሎች መፈንጫ እንደሆነ ቀጥሏል ይላሉ። ለወራት ደጋግመን ብንጮህም ድምጻችንን የሚሰማ መንግስትም ሆነ ስርዓት አላገኘንም ሲሉ አማረዋል። በሞያሌ በኩል አድርጎ የኬንያውን መስመር፣ በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ በኩል በወረራ የጅቡቲን የባቡር ሃዲድ ለመቆጣጠር የስግብግብነት ባህርይው አሸንፎት ለመስፋፋት ተደጋጋሚ ሙከራ የሚያደርገው የኦሮሙማ ተስፋፊ ኃይል አካሄድ ለኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ ነው። በሸዋ ይፋት፣ አጣዬ፣ ሸዋሮቢትና አካባቢው በስንቅ እና በትጥቅ ተደራጅቶ በቡድን መሳሪያ ጭምር አማራዎችን በጭካኔ እየጨፈጨፈ፣ እያፈናቀለና እየዘረፈ ያለው ኦነጋዊ የሽብር ቡድን ሀገርን በተለያዩ አቅጣጫዎች በተለይም በአማራ፣በደቡብ፣በሲዳማ፣በአፋር እና በቤንሻንጉል በኩል እያደረገው ያለው የአፍራሽነት እንቅስቃሴ ብዙዎችን ያሳሰበና ለከፍተኛ ፈተና እየዳረገ ያለ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። ድብቅ ሴራ እየተከናወነ እያዬ እንዳላዬ የሚያልፈው እና እያሻሻጠ ያለው አመራር ጉዳይም በአሳሳቢነቱ ቀጥሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በማኦኮሞ ወረዳ ጉዳይ እየቀረበ ላለው ተደጋጋሚ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ በሚል የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልን ፕሬዝደንት አቶ አሻድሌ ሀሰንን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱን አቶ ጌታሁን አብዲሳንና የአሶሳ ዞን የብልጽግና ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱን ለማግኘት ጥረት አድርጓል። አቶ ጌታሁን አብዲሳ ስልካቸውን አንስተው ቅሬታውን ከሰሙ በኋላ ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አሁን አይመቸኝም በማለት ስልክ ዘግተዋል። በተደጋጋሚ ሲደወልላችሁ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ እየሆናችሁ አይደለም፤ የደረሰንን ቅሬታ በተናጠል ለማቅረብ እንገደዳለን በሚል ተነግረዋል። አቶ አሻድሌ ሀሰንና አቶ ይስሃቅ አብዱ የሚጠራ ስልካቸውን በመዝጋት ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም። በማኦኮሞ ወረዳ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ከፈቀዱ ሀሳባቸውን አካተን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply