You are currently viewing በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የኩጃ ወጣቶች የአድዋን በአደባባይ እንዳናከብር ተከለከልን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፤ በሰልፍ እንደሚያከብሩ ቀድመው ስላልነገሩን ከልክለናል ሲሉም የወረዳው አስተዳዳ…

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የኩጃ ወጣቶች የአድዋን በአደባባይ እንዳናከብር ተከለከልን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፤ በሰልፍ እንደሚያከብሩ ቀድመው ስላልነገሩን ከልክለናል ሲሉም የወረዳው አስተዳዳ…

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የኩጃ ወጣቶች የአድዋን በአደባባይ እንዳናከብር ተከለከልን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፤ በሰልፍ እንደሚያከብሩ ቀድመው ስላልነገሩን ከልክለናል ሲሉም የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የኩጃ ወጣቶች የአድዋን በአደባባይ እንዳናከብር ተከለከልን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፤ በሰልፍ ቀድመው ስላልነገሩን ከልክለናል ሲሉም የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል። ቅሬታ አቅራቢው እንደሚሉት ከ120 በላይ ወጣቶች ትሸርት እና ባነር አሰርተው የአድዋን በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ነበር። ይሁን እንጅ የካቲት 22/2014 የቀበሌ እና የወረዳ መስተዳድር አካላት እንዲገኙ እንዲሁም ትብብር እንዲያደርጉላቸው ቢጠይቋም ቀድማችሁ ስላላሳወቃችሁን በአደባባይ ማክበር አትችሉም የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። ቅሬታው የደረሰው አሚማ ሁለቱን አካላት በማገናኘት ችግሩ እንዲፈታ ጥረት አድርጓል። የጉራ ፈርዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ወጣቶቹ በዓሉን በሰልፍ እንደሚያከብሩ ቀድመው ስላልነገሩን በማለት አይቻልም ሲሉ መከልከላቸውን ተናግረዋል። በመጨረሻም በጉዳዩ ዙሪያ የካቲት 23 ቀን 2014 ጠዋት ላይ ከአካባቢው የመስተዳድር አካላት ጋር እንዲነጋገሩና ባነራቸውን፣ ቲሸርታቸውንና መልዕክታቸውን እንዲያሳዩ ሲሉ አቶ ሲሳይ ፈቅደዋል። በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ያገኙታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply