በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ህዳር 01 ለህዳር 02 አጥቢያ ሁለት አማራዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ            አሸዳራ ሚዲያ        ህዳር 02 / 2013…

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ህዳር 01 ለህዳር 02 አጥቢያ ሁለት አማራዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ አሸዳራ ሚዲያ ህዳር 02 / 2013…

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ህዳር 01 ለህዳር 02 አጥቢያ ሁለት አማራዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ አሸዳራ ሚዲያ ህዳር 02 / 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ነዋሪዎቹ ከቦታው እንዳረጋገጡልን በጉራ ፋርዳ ወራዳ ሆጀንታ ቀበሌ ትናንት ሌሊት ሁለት አማራዎች የተገደሉ ሲሆን ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም አስራ ስድስት የሚደርሱ የአማራ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን ገልጸውልናል፡፡… እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ ከአሁን በፊት በግፍ የተገደሉ አማራዎች ጉዳይ ምንም አይነት መፍትሄ ያላገኘ ሲሆን ከአካባው የተመረጡ ግለሰቦች ጥቃት ለመመከት በሚል ወደ ጉራ ፋርዳ ወረዳ ሄደው ትጥቅ ሊሰጣቸው እንደሆነ መረጃው የደረሳቸው ጽንፈኞች ግድያውን ሊፈጽሙ ችለዋል ብለዋል፡፡ በጉራ ፋርዳ ወረዳ አማራዎች አሁንም አስከፊ ችግር ውስጥ የገቡ ሲሆን ከጤና እና መሰረታዊ ፍላጎቶች ፍጆታ በተጨማሪ የደህንነታቸው ስጋት አይሎብናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመበትን የጉራ ፋርዳ ወረዳ ሆጀንታ ቀበሌ አስተዳዳሪ ለማግኘት ያደረግነው የስልክ ሙከራ ባለመሳካቱ አሁን ላይ በቀበሌው የደረሰውን የግድያ እና የጉዳት መጠን በውል ለመለየት አልቻልንም፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply