
“በብልጽግና ች ትዕዛዝ ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ምስክር ሆነው ያሳሰሩን 8 የገንዳውሃ ልጆች በዋስትና ተለቀናል” ሲሉ ተፈችዎች ተናገረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በብልጽግና አመራሮች ትዕዛዝ ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ምስክር ሆነው ያሳሰሩን 8 የገንዳውሃ ልጆች በዋስትና ተለቀናል” ሲሉ ተፈችዎች ለአሚማ ተናገረዋል። መጋቢት 29/2015 በተደረገው ብልጽግናን ባወገዘው የተቃውሞ ሰልፍ ተሳትፋችኋል፣ አስተባብራችኋል በሚል ከ3 ሳምንት በኋላ ሚያዝያ 23/2015 በብልጽግና ካድሪዎች ትዕዛዝ በጸጥታ አካላት ተይዘው በገንዳውሃ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ ታስረው ስለመቆየታቸው ተናግረዋል። አሚማ ያነጋገራቸው ምጭ እንደገለጹት “ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ምስክር ሆነው” ያሳሰሯቸው 8 የገንዳውሃ ልጆች ግንቦት 2/2015 እያንዳንዳቸው በ3 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተዋል። ከእስር የተፈቱትም:_ 1. አንተነህ ቀለመወርቅ፣ 2. ክብሮም ሞላ፣ 3. ቶፊክ ሳልህ፣ 4. ታየ አበጋዝ፣ 5. አበበ አብርሃም፣ 6. ዮናስ ቆያቸው፣ 7. አብርሃም ሸጋው እና 8 ኀይሌ አረጋይ የተባሉ የገንዳውሃ ልጆች ናቸው።
Source: Link to the Post