በብራዚል ቦልሰናሮን ደግፈው የምርጫውን ወጤት ተቃውመው በወጡ ሰልፈኞች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ህዝቦች ሲሰጡ የነበረው ሰላምታን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራ ድረ ገጾች ከተለቀቀ በኋላ ምርመራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በምርጫ ውጤቱ ተቃውሞ በቦልሰናሮ ደጋፊዎች በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ሰልፈኛው የናዚን ሰላምታ ሲሰጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ምርመራ ምክኒያቱ ደግሞ በብራዚል የናዚን ሰላምታ እንደ ጥላቻ ወንጀል ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው ሲል የዘገበው አርቲ ኒውስ ነው፡፡
በብራዚል በተደረገ ምርጫ ሉላ ዳሲልቫ ማሸፋቸው አይዘነጋም፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply