በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ፍ/ቤት የ10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደየአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ያየ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/CNGF2DNQhiAyVyd5pVOVTUuuJrXyo32ztN5qcHBVCtCk305Ef-8-R7UsaaRQ6xmDZtK_VY4J-4GB4YMUKTcmIyGg_9jFV_zbUqu5KGiJb72xADFMM0mh6EncbYdcyTOlMYXlYdTkk9_VLLzaFA_vM1mJSi5sO85K9yT1_seO1I9Nrghgqg33CU2OO1EJrjSK9bMNh2kA9YMCmGN2LKu8PN4yIySugBfAia0h-0aCB6lEaLxybc7FT52AlTAcHyWRImAobTc9vTVdq-GVmQd9HxfhbFEVRQy7CK97ObEV2bO-RHJddrvhAVYMZPia8_cxlAwkl265WYKBjyfUi8e4zQ.jpg

በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ፍ/ቤት የ10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ያየ ሲሆን የመርማሪ ቡድኑ ምርመራየን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መረጃው የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ ያን ያህል ጊዜ ስለማይዎስዱ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል በዚህ ምክኒያት በእስር ሊቆዩ እና የጠየቅነው የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ስላመነበት የምርመራ ቡድኑ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀናት ብቻ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሰኔ 2/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

(አብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply