በብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የተጻፈ ሸማቂው ኮማንዶ” መጽሐፍ ተመረቀ።               አሻራ ሚዲያ          ጥር፡-09/05/13/ዓ.ም ባህ…

በብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የተጻፈ ሸማቂው ኮማንዶ” መጽሐፍ ተመረቀ። አሻራ ሚዲያ ጥር፡-09/05/13/ዓ.ም ባህ…

በብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የተጻፈ ሸማቂው ኮማንዶ” መጽሐፍ ተመረቀ። አሻራ ሚዲያ ጥር፡-09/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር በመጽሐፉ የብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞና የጓዶቻቸው እውነተኛ የህይወት ተሞክሯቸውን የያዘ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የህይወትን የውጣ ውረድ ፍትጊያ፣ ተልዕኮ፣ ውድቀትና ስኬት ለመከወን፣ ስውተረተር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጡኝ ወላጆቼ አባቴ ማሞ ጨርቆስ እና እናቴ ፈንታዬ በምስጋናው እንዳስቀመጣቸው አብራርቷል፡፡ በብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ሸማቂው ኮማንዶ በሚል ርዕስ የታተመው መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ እንደገለፁት በመጽሐፋቸው ከውልደት እስከ እድገት ብሎም ከውጣውረድ እስከ ስኬት ያለውን ታሪካቸውን እንደከተቡበት በመድረኩ አስተዋታውቀዋል። የማውቀውን ታሪክ ለትውልድ ባለማሻገር የህሊና ተጠያቂ ላለመሆን ነው መጽሐፉን የጻፍኩት ሲሉም ጀነራሉ ተናግረዋል ። የህይወት ልምድና ተሞክሯቸውን ያሰፈሩበት ይህ መጽሐፍ የኪነጥበብ ሰዎች ፣ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በተገኙበት ተመርቋል። በመጽሐፍ ምረቃው የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እንደገለጹት ያልተነገሩ ታሪኮቻችን መጻፍ ይገባል። ጀኔራሉ ያላቸውን ልምድና እውቀት ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል ኮሚሽነሩ። መጽሐፉ ልዩ ልዩ ታሪኮችና ጀብዶች ሰፍረውበታል ያሉት ደግሞ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር ዶክተር ፈንታሁን አየለ ናቸው፡፡ ትክክለኛ ታሪኮች ከባለታሪኮች ሲቀርብ ተጨባጭ ይሆናልና ሌሎችምን ያስተምራል ሲሉ ዶክተር ፈንታሁን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም መፅሃፉን ለመፃፍ ከሁለት ዓመት በላይ እንደወሰደባቸው ተናግረዋል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply