በብአዴን መዋቅር ውስጥ ጎጠኝነትና ጥቅመኝነት እንጂ ሐቀኝነት አሸንፎ አያውቅም ነበር! አሳየ ደርቤ ባህርዳር:- የካቲት 25/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ዛሬ ግን የአ…

በብአዴን መዋቅር ውስጥ ጎጠኝነትና ጥቅመኝነት እንጂ ሐቀኝነት አሸንፎ አያውቅም ነበር! አሳየ ደርቤ ባህርዳር:- የካቲት 25/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ዛሬ ግን የአቶ ጸጋ መራር እውነት የጥቅምን እና የጎጥን ሰንሰለት በጣጥሳ ማሸነፍ ቻለች። እናም ብድር በሚል ሥም ከአሠራር ውጭ 60 ሚሊዮን ብር የተከፋፈሉ አመራሮች ከእነ ወለዱ እንዲከፍሉና ከሥልጣናቸው እንዲታገዱ ተወስኗል። የአማራ ብልፅግና አመራርና ባለሙያዎች በህገ ወጥ መንገድ የተከፋፈሉትን ብር እንዲመልሱ፣ከሀላፊነታቸውም እንዲታገዱ ፓርቲው ውሳኔ አሳልፏል። “…… በብድር ስም የወጣው የፓርቲው ገንዘብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከነ ወለዱ ታስቦ ተመላሽ እንዲደረግና ዝርዝር ሁኔታው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በብድር ስም ገንዘብ የወሰዱ አመራርና ሰራተኞችም ከያዙት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነት ከየካቲት 25/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ሆኖም ለአሰራሩ ተገዥ በመሆን ተፈፃሚ የማያደርጉ ግለሰቦች ካጋጠሙ በህጉ መሰረት ተጠያቂነታቸው የሚከናወን ይሆናል፡፡” ሲሉ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ሀሳባቸውን አንፀባርቀዋል ብሏል። ፀጋ አራጌ አንዱን በድል አሸንፏል! አንድ አመራር የወሰደውን 8.9 ሚሊዮን ብር ለመመለ (ከደመወዙ አንፃር ሲሰላ) 112 ዓመት ይፈጅበታል ይላሉ የባንክ ባለሙያዎች😁😃😃😃 የአማራ ብልፅግና 16 አመራር እና ባለሙያዎችን ከስራ ማገዱ ታወቀ። እነዚህ የአማራ ብልፅግና ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎች የታገዱት ከወራት በፊት የፓርቲውን ገንዘብ በብድር ስም በህገ ወጥ መንገድ ተከፋፍለውት በመገኘቱ ነው።አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ በተደረገው ማጣራትም ገንዘቡን መውሰዳቸውን ተረጋግጧል። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እነዚህ አካላት ገንዘቡን እስከ ወለዱ እንዲመልሱም የቀነ ገደብ አስቀምጧል። የእግድ እና የገንዘብ ማስመለስ ደብዳቤው ተያይዟል። መለከት ሚዲያ በደረሰው ዝርዝር መሰረት አንድ ሰው ከዝቅተኛው ከ370ሺህ ብር እስከ 8.9 ሚሊዮ ብር ከፓርቲው ወጭ አድርጎ ወስዷል ሲል ደግሞ መለከት Media ዘግቧል https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=534874407994181&id=100044148803693 ምርመራ:- ብአዴን ፈደራል ላይ ያሉትን ዘረፊ አባሎቹን ለጊዜው እንዳላገዳቸው ታውቋል። ዋነኞቹን ትቶ ዝቅተኛ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ማገድ የፈሪነት ምልክት ነው ሲል አማራ ብሎገር ዘግቧል ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply