You are currently viewing በቦሌ ቡልቡላ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ከሰሞኑ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እንቅስቃሴ አኳያ ከ30 በላይ ወጣቶች ታፍነው ወደየት እንደተወሰዱ ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በቦሌ ቡልቡላ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ከሰሞኑ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እንቅስቃሴ አኳያ ከ30 በላይ ወጣቶች ታፍነው ወደየት እንደተወሰዱ ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በቦሌ ቡልቡላ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ከሰሞኑ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እንቅስቃሴ አኳያ ከ30 በላይ ወጣቶች ታፍነው ወደየት እንደተወሰዱ ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በቦሌ ቡልቡላ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ከሰሞኑ በተለይም ከየካቲት 1/2015 ጀምሮ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በማያያዝ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶች ታፍነው ወደየት እንደተወሰዱ ለማወቅ አለመቻላቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መረጃ ያደረሱ ቤተሰቦች ተናግረዋል። በቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሰነበቱ በኋላ የካቲት 6/2015 ከቀኑ 5 ጀምሮ በአውቶብስ ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው ተገልጧል። በመንግስት የጸጥታ አካላት ታፍነው አድራሻቸው የት እንደሆነ ካልታወቁት ከ30 በላይ የቦሌ ቡልቡላ ወጣቶች መካከልም:_ 1) አዕምሮ የኔነህ፣ 2) ስማቸው ተፈራ፣ 3) ሰው አትመን የኔነህ፣ 4) አደመ ወንድምነህ፣ 5) ታመነ አበባው እና 6) እንዬው ዳኛቸው የተባሉ የአማራ ተወላጆች ይገኙበታል። የታሳሪ ቤተሰቦችም ባይሆን የልጆቻችን አድራሻ ይንገሩን ሲሉ በመማጸን ላይ ናቸው። ፎቶው_ 1) የአዕምሮ የኔነህ_ባለመስቀሉ፣ 2) አደመ ወንድምነህ፣_ባለፊደል ቲሸርቱ፣ 3) ስማቸው ተፈራ_ሱፍ የለበሰው፣ አማራ ሚዲያ ማዕከልን ይደግፉ! ሙሉ መረጃውን በሚከተለው የዩቱብ አድራሻ ለማግኘት ይችላሉ:_ https://youtube.com/@amaramediacentre

Source: Link to the Post

Leave a Reply