በቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም በተነሳ የእሳት አደጋ የስድስት አመት ህጻን ህይወቱ አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቦሌ አራብሳ…

በቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም በተነሳ የእሳት አደጋ የስድስት አመት ህጻን ህይወቱ አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም በተነሳ የእሳት አደጋ የስድስት ዓመት ህጻን ህይወቱ ሲያልፍ ከአደጋው ለማምለጥ ከህንፃ የዘለለችው ግለሰብ የአካል ጉዳት ደርሶባታል። የካቲት 17 ቀን 2014 ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ከሀያ ደቂቃ ላይ አራብሳ ኮንደሚኒየም ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የስድስት አመት እድሜ ያለው ህጻን ህይወቱ ሲያልፍ እድሜዋ 10 አመት የሆነች የሟች እህት በጭስ የመታፈን አደጋ እንደረሰባት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አራብሳ ኮንደሚኒየም ብሎክ ሰላሳ አራት 5ኛ ፎቅ ላይ አደጋው መድረሱን ገልፀዋል። አደጋው ሲደርስ በጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትኖር የ18 አመት እድሜ ያላት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ከ5ኛ ፎቅ ላይ ዘላ ራሷን ለማዳን ባደረገችዉ ሙከራ ከባድ ጉዳት እንደረሰባት ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በእሳት አደጋዉ 50 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም የእሳት አደጋ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ተዛምቶ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ እሳቱን መቆጣጠር ችለዋል። በኮንዶሚኒየም ቤቶች አልፎአ ልፍም ቢሆን አደጋዉ እያጋጠመ በመሆኑና የአደጋዉ ምክንያትም በአብዛኛዉ ኤሌክትሪክ በመሆኑ በኤሌክትሪክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲረግና የኤሌክትሪክ መስመሮቻችን በባለሞያ ማስፈተሽ እንደሚያስፈልግ አቶ ንጋቱ አሳስበዋል፡፡ የዛሬዉ የእሳት አደጋም በኤሌክትሪክ ምክንያት የተነሳ እንደሆነ ገልፀዋል። የኮንደሚኒየም ቤቶች የአደጋ ጊዜ ማምለጫ ደረጃዎችም ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ኮሚሽኑ አስታውቋል ያለው ብስራት ራዲዮ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply