በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታ አንበሳ ጋራጅ ጀርባ በሚገኝ ህንጻ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ዛሬ ሰኞ ከቀኑ 8:49 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/gfxf4Lx3dSs4-bEKwEuzfB5SP-EAVCNGt7TuHC1MxeD3_Sg86J8Lh8dAEgVYMwEFZuE2jC9UXhYx0JGfXKN9SJ15L3ASi4gUqneQ_06gpIHz10-u4RR6XTudRCvH94JXqtsv7mbScAJ0QTFfjhITI_dE6lSOXEk-0nRzvSrWnsnjKjPzLaAeZX8GT1BTu5CAPg6jaTH3bA42ZVU8bGrJHlKC4l5VL2Zs_jO-coO3OJxTkQIctQNB_SzCS7LoN_tNMxDZtKqmETIS4UdEHBsywQFtQdnhBS7JJNMfulLR0-F2Wwv6b1broRoRvQryxqA1LWI4TxZs_9kNXqqbhHJs0w.jpg

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታ አንበሳ ጋራጅ ጀርባ በሚገኝ ህንጻ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

ዛሬ ሰኞ ከቀኑ 8:49 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታ አንበሳ ጋራጅ ጀርባ ባለስድስት ወለል ህንጻ በሆነዉ በስሪ ሳይ ኮሌጅ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 1 ሚሊየን 500 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም 300ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ተችሏል።

የእሳት አደጋዉ ሲደርስ በህንጻዉ ዉስጥ የነበሩ ሶስት ሰዎችን የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጉዳት ሳይደርስባቸዉ ሶስቱንም ሰዎች መታደግ ከህንጻዉ ዉስጥ አዉጥተዋቸዋል።
የእሳት አደጋዉ የተነሳዉ ከ3ኛ ፎቅ ላይ ሲሆን ወደሌሎች ወለል ሳይዛመት መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት አደጋዉን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር 1ሰዓት ከ23 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የኮሚሽኑ የኮሚኒዩኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply