በቦስተን የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተኑ የቤት ውስጥ ውድድር አንጸባራቂ ውጤቶች አስመዘገቡ።

ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር እንዲሁም ለሜቻ ግርማ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድሮችን በአንደኝነት አጠናቀዋል።

የአንድ ሺህ ሜትር የዓለም ሻምፕዮና ጉዳፍ የቦስተኑን ውድድሩን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በአንደኝነት ፈጽማለች።

በዚሁ ርቀት አትሌት ብርቄ ኃየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሁለተኛነት ጨርሳለች።

የ18 ዓመቷ ብርቄ ኃየሎም ያስመዘገበችው ሰዓት በርቀቱ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።

አትሌት ለሜቻ ግርማም የቦስተኑን 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የቤት ውስጥ ውድድርን በ7 ደቂቃ 29 ሰከንድ ከ08 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ማሸነፉ ተዘግቧል።

ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply