በቫይታሚን ያልበለፀገ የስንዴ ዱቄት እና የምግብ ዘይቶች ወደ ሃገር እንዳይገቡ ተከለከሉ

(አዲስ ማለዳ፣ ህዳር 24፡ 2016)
ስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይት አስመጭዎች የሚያስገቡት ምርት በቫይታሚን ማበልጽግ (Fortification) የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ CES 309 እና CES 310 ወጥቶላቸው እንዲተገበሩ የአንድ ዓመት የትግበራ የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቶ ከሀምሌ 2015 ጀምሮ አስፈላጊውን የደረጃ መስፈርት አሟልተው ወደ ገበያ እንዲገቡ በኢትዮጵያ የደረጃወች ካውንስል መወሰኑ ይታወቃል፡፡
ይሁንና የንግድ ሚንስቴር አደረግኩ ባላቸው የኢንስፔክሽን ስራዎች በአንዳንድ አስመጪዎች አማካኝነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡት የስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይት ምርቶች በተቀመጠው የፎርትፊኬሽን አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መሰረት በቫይታሚን ሳይበለጽጉ ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑና ለዚህም በምክንያትነት የሚገለጸው ምርቶቹ በብዛት በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ እንደሆነ ደርሼበታለሁ አለ። ስለሆነም አስመጪዎች አስገዳጅ ደረጃው ተረድተው የሚያስገቡትን ምርት በቫይታሚን የበለፀገ እንዲሆን አሳስቧል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነዚህን ምርቶቹን በቫይታሚን ሳያበልጽጉ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ከአሁን በኋላ እንደማይቻል መሆኑን አስታውቃል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply