በቬንዝዌላ  ፕሬዝደንቱን ለመግደል የተጠረጠሩ 32 ሰዎች ታሰሩ ።የፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመሆን ፕሬዝደንቱን የመግደል  ሴራ አቀነባብረ…

በቬንዝዌላ  ፕሬዝደንቱን ለመግደል የተጠረጠሩ 32 ሰዎች ታሰሩ ።

የፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመሆን ፕሬዝደንቱን የመግደል  ሴራ አቀነባብረዋል በሚል ተከሰዋል ።

በሴራዉ ተካፍለዋል የታባሉ 32 ወታደሮችና ሲቢሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የቬኑዝዌላ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ታረክ ዊሊያም ሳብ ማኅበራዊ አንቂዎች፤ ጋዜጠኞች እና ወታደሮችን ጨምሮ በሌሎች 11 ሰዎችና በሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ላይም ተጠንስሶ ነበር ላሉት ሴራ የእስር ማዘዣ እንደተቆረጠባቸው ተናግረዋል።

ሳብ፣ ተጠርጣሪዎቹ ለመገናኛ ብዙሃን ስለዕቅዳቸው ተናዝዘዋል፤ መረጃዎችን አውጥተዋልም ብለዋል። ማዱሮ ትናንት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫም የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የእሳቸውን ሕግ ችላ ብለው ከአሜሪካን ጋር እየሠሩ ነው በማለትም ከሰዋል።

የዛሬ ስድስት ዓመት ማዱሮ በድጋሚ መመረጣቸውን ይፋ ባደረጉ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ሃገራት ምርጫውን አሳፋሪ በማለት ውድቅ አድርገውት ነበር።

ምንም እንኳን ዘንድሮ በሀገሪቱ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ እንደሚካሄድ ማዱሮ ቃል ቢገቡም ዋነኛዋ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ በሙስና እና በአሜሪካ ይደገፋሉ በሚል በቀረበባቸው ክስና ወንጀል ምክንያት ከተሳትፎ ታግደዋል።

ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply