በተለምዶ ካሳንቺስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አከባባቢ በአንድ ጁስ ቤት እና ሱፐር ማርኬት ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው በተለምዶ ካሳንችስ ቶታል ተ…

በተለምዶ ካሳንቺስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አከባባቢ በአንድ ጁስ ቤት እና ሱፐር ማርኬት ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው በተለምዶ ካሳንችስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ ጁስ ቤት እና ሱፐር ማርኬት ላይ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰአት በኋላ 9 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተከሰተው የእሳት አደጋ በሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም።

በንብረት ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን መጠኑ ገና አለመታወቁን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የደረሰውን አደጋ ለመቆጣጠርም አምሰት የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች እና አንድ አንቡላንስ በመያዝ የአደጋ ስጋት ሰራተኞች በቦታው ላይ እንደተሰማሩ ጠቁመዋል፡፡

የእሳት አደጋው የተከሰተበት አከባቢ የንግድ ማዕከላት የሚገኙበት እንደመሆኑ በቅርብ አቅራቢ ወደ ሚገኙት የንግድ ማዕከላት እና መስጊድ ሳይዛመት እሳቱን ሁለት ሰአታትን በፈጅ ጥረት መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ለተከሰተው የእሳት አደጋ መነሻ ምክንያት ለጊዜው አለመታወቁን እና ፖሊስ መነሻ ምክንያቱን እየመረመረ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸዉ

Source: Link to the Post

Leave a Reply