በተርክዬ የማቾች ቁጥር ከ33ሺህ በላይ ደረሰ፡፡በተርክዬ ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የማቾች ቁጥር ከ33 ሺህ በላይ መድረሱ ታውቋል፡፡እስካሁን ድረስ በቱርክዬ 29ሺህ…

በተርክዬ የማቾች ቁጥር ከ33ሺህ በላይ ደረሰ፡፡

በተርክዬ ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የማቾች ቁጥር ከ33 ሺህ በላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስ በቱርክዬ 29ሺህ 600 ያህል ዜጎች የሞቱ ሲሆን በጎረቤቷ ሶርያ ደግሞ 4ሺህ 500 ዜጎች መሞታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ በሶሪያ እስከ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡
ባሁኑ ሰአትም 900 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ነው ያስታወቀው፡፡

አደጋው በደረሰበት ጋዚያንቴፕ አቅራቢያ የሚኖሩ ሶርያዊያን እጅግ በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመልክቷል፡፡
ጋዚያንቴፕ የተባለችው የቱርክ ግዛት፣ ከሶርያ ጋር የምትዋሰን ሲሆን በአካባቢው የሶርያ አማጺያን የሚንቀሳቀሱበት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ የማድረሱን ስራ እጅግ ከባድ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply