በተሸከርካሪ ስፒከር ገጥመው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ሰዎች ለትራፊክ አደጋ መበራከት እና ለሌቦች ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ ነው ተባለ፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Pk2JPJvLlABMUj5UkMaFytcEGfGi9_Eg8p9ayY3TmBHQVz1kv1iuUJNk_hbYEBae5gKZ4ZQ8JxRdHq_itJniQ3OqTn-mUKM2jt1g5SXDUJmEz5WkDdKU3ivFWUoSTK4puYIQVWfvixtBTVYw1Cjh3IrQaeys4s57adwRoZ6AyfZdZ-xG3Eju6rERMZuSVasMDDmCyYItA-69wCsKYkBIh7tBNhvJ1yT1CzaeI2vaybzwYXibFNAzb60h8v7GagX_Eu25Q9CxeT-dMiT82Uzfg4st--zD6PksDN0TmLK2L0J22lf4lUN-NX-e9zN9Qvw_C_PtQB1D_-5Ly5JlA4ESDQ.jpg

በተሸከርካሪ ስፒከር ገጥመው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ሰዎች ለትራፊክ አደጋ መበራከት እና ለሌቦች ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ ነው ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በመዲናዋ በሁሉም አካባቢዎች በመኪና በታገዘ ልመና እና ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ሰዎች በከተማው የትራፊክ ፍሰት ላይ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ለህክምና የሚሆን ድጋፍ እንዲደረግላቸው በመኪና የታገዘ ድጋፍ የሚጠይቁ ሰዎች መለየት እንደሚስፍልግም ገልጸዋል፡፡

ድጋፍ ጠያቂዎቹ የሚይዙት የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለመለየት የሚያስቸግር ነውም ብለዋል፡፡
ስፒከር ገጥመው በየመንገዱ ድጋፍ የሚጠይቁ ዜጎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የተናገሩት ኮምንደር ማርቆስ፣ ህብረተሰቡ ድጋፍ በሚያደርግበት ጊዜ ትክክለኛ ተረጅ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ድርጊቱ አሁን ላይ በከተማዋ ትራፊክ ፍሰት ከፍተኛ ጫና እንዲፈጠር ከማድረጉም ባሻገር ለሌቦች እድል እያመቻቹ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply