በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጉዳይ አካባቢያዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ አቋም መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒ…

በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጉዳይ አካባቢያዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ አቋም መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በስብሰባው የተሳተፈችው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ የኢኮኖሚ ፣ የአካባቢያዊ ውሕደት እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ማንፀባረቋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ገልጸዋል፡፡
ቃል አቀባዩ የስምምነቱን ዝርዝር ሂደት በተመለከተ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቷ አካል አድርጋ ከምትቆጥራት፣ ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር ወታደራዊ እና የንግድ እንቅስቃሴ ለማከናወን የሚያስችላት የባሕር በር ማግኘት የምትችልበትን ስምምነት ታኅሣሥ 22 ቀን 2016 ዓ .ም አዲስ አበባ ውስጥ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስምምነቱ ከተፈረመ ከአንድ ወር በኋላ ሂደቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጾ ነበር።

ስምምነቱ ሶማሊያን ክፉኛ ያስቆጣት ሲሆን ጉዳዩን ወደ ተባበሩት ምንግሥታት የፀጥታው ምክር ወስዳው የመወያያ ጉዳይ ሆኗል። ይህንን በተመለከተ ኢትዮጵያ ምን አቋም እንዳራመደች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ተጠይቀዋል።
ይህ ስምምነት ከተፈረመ ከአንድ ወር በኋላ ሂደቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጾ ነበር። የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ ዛሬ አንድ ወር ሞልቶታል። ገዳዩ ምን ላይ ደረሰ የተባሉት ቃል ዐቀባዩ ” የስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮች የሚሠሩ ይሆናል” ካሉ በኋላ ዝርዝሩን መቼ እንደሆን ባይገልፁም ጊዜው ሲደርስ ይገለፃል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሶማሊያ የባሕር በር በኢትዮጵያም ሆነ በሌላ አካል አይወሰድም በሚል ከሰሞኑ አስተያየት ስለሰጡት ትውልደ ሶማሊያዊት አሜሪካዊት ኢልሃም ኦማር መንግሥት ምን ይል እንደሆን የተጠየቁት ቃል ዐቀባዩ “የግለሰብ አስተያየት ነው” ሀገር ለእንዲህ ያለው አስተያየት ምላሽ አይሰጥም ብለዋል።መንግሥት ከኢትዮጵያ በተለያየ ወቅት ተዘርፈው የወጡ ቅርሶችንና ሐብቶችን ማስመለሱን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል ሲል ዶቼ ቬለ ዘግቧል

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply