
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኒዮርክ የሚገኘው ቢሮ ዳይሬክተር የነበሩት ግለሰብ ከስልጣናቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
ሚድል ኢስ ሞኒተር እንደዘገበው ለዳይሬክተሩ ክሬግ ሙክቢር ከስልጣናቸው መልቀቅ ከእስራኤል እና ከሃማስ ጦርነት ጋር የተገናኘ ነው፡፡
ሙክቢር እስራኤል ከሃማስ ጋር እያደረገች በምትገኘው ጦርነት እስራኤል በሰላማዊ የፍልስጤም ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመች ነው በማለት የሰላ ትችት መሰንዘራቸው ተዘግቧል፡፡
ይህም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መርሆችን የጣሰ እና በምንም አይነት መንገድ ተቀባይነት የሌለው ነው በሚል በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣናቸው ለቀዋል፡፡
ክሬግ ሙክቢር የእስራኤልን የአምባገነንነት ስርዓትን እንደማይቀበሉ እና ከፍልስጤም ህዝብ ጎን እንደሚቆሙ መገለጻቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post