
“በተናጠል የምንሞትበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል፤ አንድ ላይ በመቆም ጠላቶቻችንን እንታገል” ሲሉ የአማራ ፋኖ በሸዋ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ በመንግስት ሃይሎች የተቀነባበረ ሴራ የአማራ ፋኖ፣የአማራ ልዩ ሃይል እና የአካባቢው ህዝብ በመተባበር አጥፊወቻችን በፈለጉበት ልክ መሄድ እዳይችሉ አድርገው መልሰዋቸዋል ሲሉ ገልፀዋል። አጣዬ፣ጀብውሃ ፣ሰበቴ ኤፍራታ ግድም ወረዳ የደረሰው ውድመትና የአማራ ልዩሃይል ጥቃት በመንግስት አመራሮች ተዋናይነት የተፈፀመ ጥቃት ነው ሲሉ የገለፁት ፋኖዎቹ ሽዋሮቢትን ለማውደም ሽዋን ለመቆጣጠር የመጣው የኦሮሞ ሃይል በአንድነታችን ሳይሳካለት ቀርቷል ነው ያሉት። በመንግስት አመራሮች አጀንዳ እየተዘጋጀለት የሚንቀሳቀሰው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ዘመናዊ መሳሪያ በመታጠቅ እና በርካታ የሰው ሃይል በማሰለፍ በአራቱም አቅጣጫ አማራን እየጨፈጨፈ ይገኛል፤ ስለሆነም ሁሉም አማራ በአንድ ላይ ሊቆም ያገባል ብለዋል። አማራው ለበርካታ አመታት የስልጣን ጥማት ባለባቸው ከንቱዎች እና በሆዳም ወንድሞቹ ብዙ ዋጋ እየከፈለ ሲኖር የቆየ ቢሆንም በተለይም ደግሞ በእነዚህ አራት አመታት በጅምላ እየታረደ በጅምላ እየተቀበረ ይገኛል። በመሆኑም መላው አማራ በተጠንቀቅ በመቆም በህይወት ለመኖር ሊታገል ይገባል ሲሉም ጨምረዋል። አክለውም አርበኛ ዘመነ ከሴን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግና ወንድሞቻችንን ከእስር ልናስፈታ ይገባል። ሁሉም የአማራ ህዝብ ለህልውናው መታገል አለበት ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘገባው የአሻራ ሚዲያ ነው።
Source: Link to the Post