You are currently viewing በተንዛዛ አይለወጤ አሰራር የተማረሩ እና የዘር መዝሪያ ጊዜ እያለፈብን ነው ያሉ የምንጃር አርሶ አደሮች በመጋዝን ውስጥ የነበረን የአፈር ማዳበሪያን በሩን በኃይል በመስበር ተከፋፈሉ፤ በእለቱ…

በተንዛዛ አይለወጤ አሰራር የተማረሩ እና የዘር መዝሪያ ጊዜ እያለፈብን ነው ያሉ የምንጃር አርሶ አደሮች በመጋዝን ውስጥ የነበረን የአፈር ማዳበሪያን በሩን በኃይል በመስበር ተከፋፈሉ፤ በእለቱ…

በተንዛዛ አይለወጤ አሰራር የተማረሩ እና የዘር መዝሪያ ጊዜ እያለፈብን ነው ያሉ የምንጃር አርሶ አደሮች በመጋዝን ውስጥ የነበረን የአፈር ማዳበሪያን በሩን በኃይል በመስበር ተከፋፈሉ፤ በእለቱ በተተኮሰ ጥይት አንድ ወጣት ተገድሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 6/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በተንዛዛ አይለወጤ አሰራር የተማረሩ፣ በእርሻ ወቅት በየቢሮው ሲጉላሉ የከረሙ እና የዘር መዝሪያ ጊዜ እያለፈብን ነው ያሉ የምንጃር አርሶ አደሮች በመጋዝን ውስጥ የነበረን የአፈር ማዳበሪያን በሩን በኃይል በመስበር መከፋፈላቸው ታውቋል። ከታች እስከ ላይኛው የመንግስት አካላት በዩኔን መጋዝን ውስጥ የተከማቸ የአፈር ማዳበሪያ እያለ መሬታችን ጾም ሊያድር ነውና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ በመጥፋቱ የኃይል አማራጭን ስለመጠቀማቸው ተገልጧል። የተለዬ ህገ ወጥ ስራ ለመስራት ስለፈለግን አይደለም ጤፍ አምራች የሆነው የምንጃር አርሶ አደር ብልሹ እና ሙሰኛ አሰራርን የኑሮአቸው ምንጭ ባደረጉ የብልጽግና ካድሪዎች የተነሳ መሬቱ ጾም ማደር የለበትም በሚል ስሜት ከቆላማ አካባቢ አቆራርጠው የመጡ ገበሬዎች ናቸው በቅድሚያ የመጋዝን በር በመስበር ማዳበሪያ የወሰዱት። እኛ ህገወጥነትን አናበረታታም ነገር ግን ማዳበሪያ ከህይወታችን ጋር የተያያዘ በመሆኑ እና ጊዜም ስለሌለን ወስደናል፤ በቀጣይ መጥቶ የሚያነጋግረን ካለ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ እንከፍላለን እያሉ በመጋዝኑ አካባቢ ለነበሩ የመንግስት አካላት ሲናገሩ ነበር። በእለቱ በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ወረዳ መስተዳድር የጸጥታ አካላትን ስምሪት እንዳልሰጠ ቢነገርም ከየትኛው አካል እንደሆነ በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ ሀምሌ 5/2015 ወደ ከሰዓት አካባቢ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ወጣት ህይወት አልፏል። በክትቻ ቀበሌ ጀጀባ ቆላ፣በአረርቲ ከተማ እና ዘሙ አገር በተባለ የአረርቲ ዙሪያው ያሉ በርካታ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ ስለመውሰዳቸው ተገልጧል። የምንጃር ወረዳ መስተዳደር ሀምሌ 6/2015 ባደረገው አስቸኳይ የአመራር ስብሰባ በየገጠር ቀበሌዎች በመጋዝን የተቀመጠ ማዳበሪያ ነአስቸኳይ እንዲሰራጭ አቅጣጫ ስለመስጠቱ የአሚማ የመረጃ ምንጮች አስታውቀዋል። በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች በመጋዝን ውስጥ የተቀመጠ ማዳበሪያ አዘግይቶ ለነጋዴ ከመስጠት ይልቅ አርሶ አደሩ በየጊዜው እየተመላለሰ እንዳይጉላላ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል የሚል ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply