በተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ ቀበሌ ጥር 3 ቀን በጉምዝ ታጣቂዎች ከተፈፀመው ጭፍጨፋ ተርፈው የተፈናቀሉ ወገኖች በችግር ላይ መሆናቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 6 ቀ…

በተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ ቀበሌ ጥር 3 ቀን በጉምዝ ታጣቂዎች ከተፈፀመው ጭፍጨፋ ተርፈው የተፈናቀሉ ወገኖች በችግር ላይ መሆናቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 6 ቀ…

በተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ ቀበሌ ጥር 3 ቀን በጉምዝ ታጣቂዎች ከተፈፀመው ጭፍጨፋ ተርፈው የተፈናቀሉ ወገኖች በችግር ላይ መሆናቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረጉት ቅሬታ አቅራቢ እንዳወሱት ጥር 3 ቀን 2013 የጉምዝ ታጣቂዎች በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል። በእለቱም የሽብር ቡድኑ ሾፌር እና ረዳት፣ የ2 ዓመት ህጻን ልጅ፣ እናት እና ልጅን ጨምሮ 11 በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች የፊጥኝ በማሰር አንበርክኮ በጥይትና በስለት በግፍ ገድሏቸዋል። በዘር አጥፊው የጉምዝ ታጣቂ ቡድን የተገደሉትም:_ 1)ቄስ ኤፍሬም ተ/ሀይማኖት 2)የማነ ብርሀኔ 3)ይበልጣል ይስማው 4)አየው ያረጋል 5)በቀለ የማስ ትራክተር ረዳት 6)ብሩ የቀን ሰራተኛ፣ 7)አብዱ ሾፌር የማስ ትራክተር 8)ህጻን ገ/ሚካኤል እብህ 9)አስቴር አወቀ የጤና ባለሙያ 10) ወ/ሮ ሽታዬ የህጻን ገ/ሚካኤል እብህ እናት 11)ወ/ሮ ሀረጓ የቀበሌ አስተዳዳሪው የአቶ አደም ዲያስ ባለቤት ጥር 3 ቀን 2013 ንጋት ላይ ነው በግፍ የተገደሉት። የፊጥኝ ታስሮ ከወደቀበት ሚቷል በሚል ጫማውን አውልቀው ጥለውት ሄደው አንድ ለወሬ ነጋሪ ወጣትመብራቱ ተስፉ በጊዜው መትረፉ ተወስቷል። በወቅቱ ከጭፍጨፋው ተርፈው ከቀያቸው የመፈናቀል እጣፈንታ የገጠማቸው አባዎራና ህጻናትን ጨምሮ በድምሩ 38 ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በአልመሃል በአንድ ግቢ ውስጥ ባሉ 5 ጠባብ ክፍሎች ውስጥ በችግር ላይ ይገኛሉ። ከፍተኛ የሆነ ለኮሮና ተጋላጭነት ስጋት፣ የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለባቸው ተገልጧል። የተፈናቃዮች ስም ዝርዝርም:_ 1)ፀጋዬ ለማ 5 ራሱን፣ 2)መንግስቱ ገ/እየሱስ 5 ራሱ፣ 3)ቄስ ፍሬው ብርሃኑ 3 ራሱን፣ 4)አወቀ ጌታሁን 3 ራሱን፣ 5)ስንታየሁ 4 ራሱን፣ 6)መብራቱ ተስፉ 3 ራሱን (ሞቷል ተብሎ ተጥሎ ከሞት የተረፈ)፣ 7)እብህ ዮሃንስ/ ባለቤቱና ህፃኑ ልጁ የተገደሉበት/ 8)ወ/ሮ ፈንታነሽ 2 ራሷን፣ 9)ሙሉቀን መልካሙ፣ 10)ችሎት ፈንቴ፣ 11)ሞገስ፣ 12)ወ/ሮ አዲሴ 13)ትዕግስት 2 ራሷን፣ 14)ቸሬ 2 ራሱን፣ 15)አለምነሽ 2 ራሷን፣ (የሟች የቄስ ኤፍሬም ባለቤት) 16) አቶ ዘለቀ 2 ራሱን፣በድምሩ 38 ሰዎች ሀብት ንብረታቸው ወድሞ ተፈናቅለዋል። ለሁለት ወር በሚል ለአንድ ቤተሰብ እስከ 30 ኪ/ግራም ስንዴ ቢሰጥም የነቀዘና የተበላሸ በመሆኑ ለምግብ አገልግሎት ለማዋል መቸገራቸውን የገለፁት ቅሬታ አቅራቢው ከፍተኛ የሆነ የመጠጥ ውሃ ችግር አለብን ብለዋል፤ አንድ በርሚል ውሃ እስከ 40 ብር ለመግዛት ተገደናል ሲሉም አክለዋል። ኮማንድ ፖስቱና የቀበሌ መስተዳድሩም ችግሩን ለመፍተታ አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተሰብ ለመንቀሳቀስ እንኳ ሊፈቅዱልን አልቻሉም ሲሉ አማረዋል። የአልመሽመሽ ቀበሌ አስተዳዳሪን አድራሻ እንዳገኘን ምላሻቸውን አካተን የምንቀርብ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply