በተከዜ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ በጥበቃ ላይ ሳሉ በህወሀት ተኩስ የተከፈተባቸው 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ከቀናት የጫካ ቆይታ በኋላ በሰላም አዳርቃይ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በተከዜ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ በጥበቃ ላይ ሳሉ በህወሀት ተኩስ የተከፈተባቸው 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ከቀናት የጫካ ቆይታ በኋላ በሰላም አዳርቃይ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በተከዜ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ በጥበቃ ላይ ሳሉ በህወሀት ተኩስ የተከፈተባቸው 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ከቀናት የጫካ ቆይታ በኋላ በሰላም አዳርቃይ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህወሀት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ መቀሌን ጨምሮ በዳንሻ፣በበአከር፣በብድብዴ፣በሶሮቃና በሌሎችም አካባቢዎች በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ አሳዛኝና አሳፋሪ የተባለ የክህደት ጥቃት መፈፀማቸው መገለፁ ይታወሳል። ይህን ህወሀት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ብሎም በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በማፀደቅ ህግ የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑም አይዘነጋም። እየተደረገ ባለው የተኩስ ልውውጥም የመከላከያ ሰራዊት፣ እንዲሁም ህወሀት ጥቃት በፈፀመባቸው የአማራ አካባቢዎችም ከአማራ ልዩ ሀይል፣ከአማራ ፋኖዎች፣ከሚሊሻ፣ፀረ ሽምቅና ከአርሶ አደሮች ጋር በመተባበር ህወሀትን ድባቅ በመምታት ማክሰኞ ገበያ/ከተማ ንጉስ፣ ዳንሻ፣በአከር፣ብድብዴ፣ባናት፣የሁመራ ሱዳን መንገድንና የሁመራን አየር ማረፊያን ጭምር መቆጣጠራቸውና በርካታ የህወሀት ሚሊሻዎችም እጅ ስለመስጠታቸው ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እየተሰጡ ያሉ መረጃዎች አመልክተዋል። በተያያዘ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ጥቃት ከተከፈተባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪም በተለያዩ ተቋማት ጥበቃ ላይ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላትም ይገኙበታል። ከእነዚህም መካከል በተከዜ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ይገኙበታል። ከተከፈተባቸው ተኩስ ራሳቸውን በመከላከል ከቀናት በጫካ የእግር ጉዞ በኋላ ዛሬ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ በሰላም መግባታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። አንደኛውን የፌደራል ፖሊስ አባል በቀጥታ የስልክ መስመር አግንተን ለማናገር ያደረግነው ሙከራ ኃላፊዬ ሲፈቅድ እሰጣለሁ በማለቱ ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply