በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ዳይሬክተር አቶ ኢብራሂም ተካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤በያዝነዉ የ2016 ዓመት የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የሚያገኙ ዜጎችን ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን ነግረዉናል፡፡
ኃላፊዉ ባለፈዉ ዓመት መደበኛ ባልሆነ ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ የተሰማሩ 2ሚሊየን 2 መቶ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ማግኘታቸዉን አስታውሰዋል፡፡
በዚህኛዉ ዓመት 10 በመቶ ጭማሪ በማድረግ 2.3 ሚሊዮን ዜጎችን በስርዓቱ ለማቀፍ ታቅዷል ብለዉናል፡፡
በመዲናዋ በ2009 ዓ.ም በሙከራ ደረጃ በ10 ወረዳዎች የተጀመረዉ የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት፣ አሁን ላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባሉ በ120 ወረዳዎች ላይ እየተሰጠ እንደሚገኝም ነግረዉናል፡፡
ከጥቅምት 1 ጀምሮም አዲስ ምዝገባ እና የእድሳት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዉ፣ እስካሁን 25 በመቶ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ስርዓቱ ገብተዋል ተብሏል፡፡
አቶ ኢብራሂም እንዳሉት፣እስከ ጥቅምት አጋማሽ ደግሞ 50 በመቶ የሚሆነዉ ሰዉ ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምዝገባዉ እና የእድሳት ስራዉ እስከ ህዳር 30 ብቻ እንደሚቆይ ገልጸው፣ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉንም ሰዉ እንደማይስተናገድም አቶ ኢብራሂም አሳስበዋል፡፡
በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post