በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት የወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

የስድስቱ ጎረቤቶቻችን ኢኮኖሚ ጂዲፒ ተደምሮ የእኛን አያክልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ከለውጡ መንግስት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስድስቱ ጎረቤቶቻችን ተደምረው የእኛን ኢኮኖሚ አያክሉም ሲሉ ተደምጠዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከምክር ቤቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡ ባሉበት ሰዓት ነው

እኛ ወደ ቢሮ ስንገባ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) 86 ቢሊየን ዶላር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ግን 205 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

ከለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ትልቁ ኢኮኖሚ እንደነበራት አንስተው ዛሬ ግን 6ቱ ጎረቤት ሀገራት ተደምረው የእኛን ጂዲፒ አያክሉም ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት የወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

በአጠቃላይ ከለውጡ በኋላ 23 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከሁሉም ዘርፎች ማመንጨት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው
ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply